በገለልተኛ ሜዳ በአዲስአበባ ስታዲዮም የተካሄደው የመቀለና ፋሲል ጨዋታ እንደመጀመሪያው ዙር ዛሬም ያለ ግብ 0-0 በሆነ የአቻ ውጤት ተጠናቆ ነጥብ ተጋርተዋል፡፡
በርካታ ደጋፊዎች የታደሙበት የሁለቱ የክልል ከተማ ክለቦች ጨዋታ ረፋድ 4:10 ሲል ጨዋታው የጀመረ ሲሆን በመቐለ ከተማ በኩል ባለፈው ሳምንት በድሬደዋ ከተማ 1-0 ከተረቱበት የመጀመሪያ 11 ተሰላፊዎች ሀብታሙ ተከስተንና ዳንኤል አድሃኖምን በያሬድ ብርሃኔና አቼምፖንግ ኦሞስን በመተካት ሲገቡ ፡ፋሲል ከተማዎች ጉዳት ላይ ባለው አምሳሉ ጥላሁንና ሙሉቀን አቡሃይ ምትክ ሰይድ ሀሰንና ሄኖክ ገምቴሳን አስገብተዋል፡፡
ለተመልካች ማራኪ በነበረው በዚህ ጨዋታ ሁለቱም ቡድኖች በፈጣን የኳስ ሽግግር ፡ ለማሸነፍ በነበረ ትልቅ ተነሳሽነትና ፍላጎት ጨዋታው በተጀመረ በ2′ ነበር የመጀመሪያውን የግብ ሙከራ የተመለከትነው፡፡በዚሁ ደቂቃ ይሳቅ መኩሪያ ከርቀት አክሮ ወደ ግብ የመታው ኳስ ለትንሽ ወጀ ውጭ ሲወጣ ፋሲሎች ቀዳሚ የሆኑበት የግብ ማግባት ሙከራ ነበር፡፡መቆለዎች የተሰነዘረባቸውን ጥቃት ምላሽ የሰጡበትን ሙከራ በ4′ ፍቃዱ ደነቀ ከርቀት አመቻችቶ ያቀበለውን ኳስ ያሬድ ብርሃኔ ሞክሮት በግቡ ቋሚ ወደ ውጭ ሲወጣ በ6′ ጋቶች ፓኖም ከመሃል ሜዳ በግቡ ትዩዩ ለያሬድ ብርሃኔ ያሻገረውን ኳስ ያሬድ፡ኳስን በደረቱ አብርዶ ወደ ፋሲል የግብ ክልል ለመግባት ሲሞክር በተሰራበት ጥፋት በግምት 17ሜትር ርቀት የተገኘውን ቅጣት ምት አማኑኤል ገ/ሚካኤል በቀጥታ ወደ ግብ ሞክሮት በግቡ አግዳሚ ወደ ላይ ወጥቷል፡፡
- ማሰታውቂያ -
የጨዋታውን የኳስ ቁጥጥር በመጠኑም ቢሆን የወሰዱት ፋሲሎች በ10ደቂቃ ኤፍሬም አለሙ መቀለ የሜዳ ክፍል ያገኘውን ኳስ 2 ተከላካዮችን አልፎ ኳስን ከመረብ ጋር አገናኘ ሲባል ከተከላካዩ ጋር በነበረ ንክኪ በመቀለ ከተማ የግብ ክልል ውስጥ ሲዎድቅ ዳኛው ሁኔታውን በዝምታ ሲያልፉ የፋሲል ተጨዋቾች በዳኛው ላይ ተቃውሟቸውን ሲገልፁ የዳኛው ውሳኔም አከራካሪ ነበር፡፡በ12ደቂቃ ተከላካዩ ሰንደይ ምትኩ በመቀለ የግብ ክልል ያገኘው ኳስ ጥሩ የሚባል ቢሆንም ሳይጠቀምበት ባክኗል፡፡በመከላከሉ ጥሩ የነበሩት መቀለዎች በረጂሙ ወደ ፊት በሚጣሉ ፈጣን የመልሶ ማጥቃት አጨዋወት በደቂቃ ጋቶች ፓኖም ከያሬድ ብርሃኔ የተሻገረለትን ኳስ ወደ ግብ ሞክሮት በግቡ አግዳሚ ወደ ላይ ሲዎጣ፡በ45ደቂቃ በአማኑኤል አማካኝነት ከግብ ክልል ውጭ ባደረጉት ሙከራ ለእረፍት ሲወጡ ፋሲሎች በርካታ ኢላማቸውን ባልጠበቁ ሙከራዎች ለእረፍት ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል፡፡
በሁለተኛው አጋማሽ ፋሲል ከተማ የአጥቂ ክፍሉን ለማጠናከር አብዱራህማን ሙባረክን በፍሊኘ ዳውዝ ቀይረው ሲያስገቡ በመቀለዎች በኩል የተጨዋች ለውጥ አልነበረም፡፡በረጃጂምና ፈጣን የኳስ ሽግግር የቀጠለው ይሄው ጨዋታ በ46ደቂቃ አማኑኤል ለመቀለ ከተማ ጥሩ የግብ ሙከራ ሲያደርግ የሁለተኛው አጋማሽ ቀዳሚ ሙከራ ሲሆን በ48 ‘ያሬድ ብርሃኔ በፋሲል የግብ ክልል ውስጥ ግራ መስመር ላይ ወደ ግብ የሞከረው ኳስ ሰይድ ሀሰን በቀላሉ ሲያወጣው በ50ኛው ደቂቃ ሰንደይ ምትኩ በሰራው ጥፋት መቐለዎች ያገኙትን ቅጣት ምት አመለ ሚልኪያስ ሞክሮት በቀላሉ ሳማኬ ኳስን ይዟል፡፡
በፋሲል ከነማ በኩል በጨዋታው የፈጠሩትን የግብ ዕድል ያክል ጎል አለማስቆጠራቸው ቡድኑ አሁንም የፊት መስመሩ መፍትሄ ሚሻው እንሆነ አመላካች ነበር፡፡በ60ኛው ደቂቃ መሀመድ ናስር በቀኝ ካታንጋ በኩል ከሰይድ ሀሰን የደረሰውን ኳስ በመቀለ የግብ ክልል ውስጥ አገባው ሲባል ሳይጠቀምበት ባክኗል፡፡የፋሲል ከተማው ሄኖክ ገምቴሳ በ64ኛው ደቂቃ በቅጣት ምት በሜዳው የግራ መስመር ቀኝ ጥላፎቅ በኩል ያሻማውን ኳስ መሀመድ ናስር በጭንቅላቱ ገጭቶ ግብ ጠባቂው በቆመበት ኳስ በግቡ አግዳሚ ለትንሽ ስትወጣ ፡ተቀይረው የገቡት ያሳርና ኤርሚያስ ለግብ የተቃረቡ ሙከራዎች የፋሲል የጨዋታው የመጨረሻ ሙከራዎች ሲሆኑ መቆለ ከተማዎች በ86’87’ደቂቃ ሶስት ነጥብ ለማግኘት የተቃረቡበትን ሙከራ ሲያደርጉ ግብ ጠባቂው ሳማኬ ሙከራዎቹ ወደ ግብነት እንዳይቀዬሩ ሲያመክን ጨዋታው ሌላ የግብ ሙከራ ሳይደረግበት ያለ ግብ 0-0 በሆነ የአቻ ውጤት ተጠናቆ ነጥብ ተጋርተዋል፡፡
የአሰልጣኞች አስተያየት
☞መቐለ ከተማ-ዮሃንስ ሳህሌ
በጨዋታው ተመጣጣኝ ፉክክር አድርገናል፡፡የሜዳው ምቹ አለመሆን ለተመልካች የሚፈለገውን ጨዋታ ለማድረግ አልተመቸንም፡፡2 ያለቀላቸው ኳሶችን አግኝተን አልተጠቀምንባቸውም ፡የተጨዋቾቻችን ስነምግባር በሁለታችንም በኩል ጥሩ ነበሩ፡፡ዛሬ ነጥብ ብንጥልም ከዋንጫ ፉክክሩ አልወጣንም፡፡የቅርብ ተፎካካሪዎቻችን ዛሬና ነገ የሚያስመዘግቡት ውጤት የሚጠበቅ ቢሆንም እስከመጨረሻው በፉክክሩ እንቆያለን፡፡
☞ፋሲል ከተማ-መሳይ ተፈሪ
-ወደ ሜዳ የገባነው ለማሸነፍ ነበር፡፡በሁለቱም የጨዋታ አጋማሾች ብልጫ ወስደን ነበር፡፡ፍፁም ቅጣት ምት ይገባናል አይገባንም የሚለውን ለዳኛው ትቸዋለሁ፡እንዳታስቀጡኝ፡፡በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ግብ ልናስተናግድ ተቃርበን ነበር፡ድክመቶቻችን በየጊዜው እያሻሻልን ነው፡፡በቀጣይም የፊት መስመራችን የስራችን ማዕከል ይሆናል፡፡p