የኢትዮጵያ ኘሪሜየ ሊግ 10 ኛ ሳምንት ጨዋታዎች መካከል ድሬዳዋ ከተማን በሜዳው ያስተናገደው መቐለ ከተማ በመጀመሪያ አጋማሽ ባስተቆጠሯቸው 2ግቦች ማሸነፍ ችለዋል፡፡
ልክ 9:00 ሲል የተጀመረው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ እንግዳዎቹ ድሬዎች 4-4-2 የሆነ አሰላለፍ ይዘው የገቡ ሲሆን ባለሜዳዎቹ እና ቀይና ነጭ ለባሾቹ መቀሌ ከነማዎች የመሃል ክፍል ብልጫ ለመውሰድ 4-5-1 የሆነ አሰላለፍ ይዘው የገቡ ሲሆን ወሳኞቹ ከመጀመርያ 11 አሰላለፍ 2ቁጥሩ አሌክስ ተሰማና 10 ቁጥሩ ያሬድ ከበደ በጉዳት ምክንያት ከአሰላለፍ የወጡ ሲሆኑ 25ቁጥሩ አቻምቦ አሞስ የአሌክስ ተሰማን ቦታ ተክቶ የመሃል አማካይነት ሚና የተሰጠው ሲሆን የአሞስ ቦታ ደሞ ሃይሉ ገብረየሱስ ገብቶ እንዲጫወት ተደርጓል ፡፡
በእለቱ መቀሌዎቹ ከወትሮ በተለየ የተከላካይ ክፍላቸው እና መሃል ክፍላቸው ድንቅ የሚያሰኝ ጥምረት ነበራቸው 6ቁጥሩ ፍቃዱ ደነቀ እና 25ቁጥሩ አቻምቦ አሞስ የነበረባቸው አንድነት መሃል ክፍላቸው ጠንካራ እንዲሆን የራሱ እገዛ ነበረው መቀሌዎች ገና ከ 8ኛ ደቂቃ ጀምሮ የድሬዳዋን በር ማንኳኳት የጀመሩት ሲሆን በእለቱ ጥሩ የነበረው የአሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊት የመጀመርያ ምርጫ የነበረው 14ቁጥሩ ሃብታሙ ተከሰተ በ8ኛ ደቂቃ ለአማኑኤል ያሻገረለት ያለቀለት ኳስ በጀማል ጣሰው በቀላሉ ተይዛለች፡፡
ቶሎ ቶሎ የድሬ በር የመድረስ አጋጣሚ ያገኙት መቀሌዎች አሁንም ከሃብታሙ ተከስተ የተላከለት ኳስ በ28 ደቂቃ አማኑኤል ገብረሚካኤል ሳይጠቀምበት የቀረችዋ ኳስ መቀሌዎችን ያስቆጨች ኳስ ነበረች ከዚች ኳስ በኋላ የበለጠ መነሳሳት የታየባቸው መቀሌዎቹ ከዚች ሙከራ በኋላ ደጋፊውም በደንብ ተነሳስቶ የሚገርም የኳስ ፍሰት ቢያሳዩም ኳስና መረብን ለማገናኘት ግን 45ደቂቃ ለመጠበቅ ተገደዋል በ 45ኛው ደቂቃ ላይ ከአማኑኤል ገብረሚካኤል ማይነስ የተደረገለትን ኳስ ፒስማርክ አድያንግ በግምት ከ30 ሜትር አክርሮ የመታው ኳስ የድሬ ግብ ጠባቂ ጀማል ጣሰው እያያት ከመግባት ውጪ ምንም ሙከራ አላረገባትም። ኳስ መሃል ሜዳ ተጀምሮ ከ1ደቂቃ በኋላ 14ቁጥሩ ሃብታሙ ተከሰተ ያቀበለው ኳስ 11ለባሹ አማኑኤል ገብረሚካኤል 45+1 ወደ ግብነት ቀይሮ ለእረፍት ወጥተዋል
ከ እረፍት በኋላ ስህተታቸው አርመው የገቡት ድሬዳዋዎቹ በአንፃራዊ ከእረፍት በኋላ የተሻለ ለመንቀሳቀስና ውጤቱ ለመቀልበስ ቢሞኩሩም በ 65 ደቂቃ የድሬዎቹ ሳንዲ ምትኬ አክርሮ የመታው ኳስ ከግቡ አግዳሚ ጋር ተጋጭቶ ቸመልሷል። ከእለት ወደ እለት የክለቡ የጀርባ አጥንት እየሆነ እየመጣ ያለው ኢኳቶሪያል ጊኒያዊው ግብ ጠባቂያቸው ፊሊፕ ኦቦኖ ያዳናት ኳስ የስምኦን አባይ ድሬዎች ወደ ጨዋታ የመመለስ አቅም የነበራት ኳስ ነበረች ከዚ ኳስ በኋላ ድሬዎች 2የቆሙ ኳሶች አግኝተው ፊልፕ ኦቦኖ ካዳናቸው ውጭ ይሄ ነው የሚባል ሙከራ ሳያደርጉ የወጡ ሲሆን በአንፃሩ በመድሃንየ ታደሰ አማኒኤል ገብረሚካኤል እና ፒስማርክ ከ2ግብ በላይ ግብ የሚያስቆጡሩበት አጋጣሚዎች ሲያባክኑ ተስተውለዋል። በተለይ 17 ለባሹ መድሃን ታደሰ ከበረኛው ጀማል ጣሰው ፊት ለፊት ተገናኝቶ ያመከናት ኳስ ውጤቱ ወደ 3-0 ምትቀይር ኳስ ነበረች
በሁለቱም 45ደቂቃ ኳስ በመንጠቁም ያለቀላቸው ኳሶች (ሹር ፓስ )ለአጥቂዎቹ በማድረስ ከነበረበት ንቃተ ሂሊና ተዳምሮ የነበረው ሙሉውን ሜዳ የማካለል ብቃት 14 ቁጥሩ ሃብታሙ ተከስተ የጨዋታው ኮኮብ የሚያስብለው እና ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ አሳይተዋል
ሌላው በሜዳው ልክ እንደ ጨዋታው አነጋጋሪ የነበረው ከንግድ ባንክ ከለቀቀ ወደ 10 ወር አካባቢ የሆነው እና ክለብ አልባ የነበረው ቶክ ጀምስ ሜዳው ላይ የተገኘ ቢሆንም በአንዳንድ ሚድያ ፈረመ የሚባለው ዜና ከእውነት የራቀና አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ለሙከራ እንደጠሩት ገልፀዋል።
የአሰልጣኞች አስተያየት
ዮሃንስ ሳህሌ የመቀሌ ከተማ ዋና አሰልጣኝ
- ማሰታውቂያ -
“ለደጋፊዎቻችን ትልቅ እውቅናና ክብር አለኝ ደጋፊዎቻችን ተጫዋቼ ሜዳ ላይ እንዲነሳሱ እና በወኔና በሞራል ተነሳስተው እንዲጫወቱ አርገውልኛል ክብር ለነሱ አለኝ ተጫዋቾቼ ላሳዩት ተጋድሎ እና ለደጋፊው ክብር ሰጥተው መጫወታቸው ለነሱም ክብር አለኝ ድሉም ለደጋፊው የገና ስጦታ ብየዋለው።” በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ስምኦን አባይ የድሬዳዋ ከተማ አሰልጣኝ
“ከእረፍት በፊት ተበልጠን ነበር፤ ስህተት እንሰራ ነበር፤ ከእረፍት በኋላ ምንም እንኳን 2-0 ብንሸነፍም እኛ የተሻልን ነበርን። ስለደጋፊው ቃላቶች ያጥሩኛል፤ በጣም ጥሩዎች ናቸው፤ ልክ በቤታችን እንደተጫወትን ነው የተሰማን። ሜዳው በጣም ይመቻል፤ ጥሩ ኳስ ይዞ ለሚጫወት ቲም በጣም ዘመናዊ ስታድየም ነው፤ ከድሬዳዋ ወጥተን አሉላ አባነጋ ከደረስን እስከ ዛሬው ጨዋታ ቤተኛ ነበር የምንመስለው ሜዳ ላይም ስማችን እየጠሩ ሲደግፉን ነበር።” በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።