በደጋፊዎች ደማቅ ውብ ዝማሬ የተጀመረው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ከጨዋታው ጅማሮ አስቀድሞ የፋሲል ከነማ ደግፊዎች ለቀድሞው አሰልጣኛቸው ውበቱ አባተ የምስጋና ሽልማት አበርክተውለታል ::
ፋሲል ከነማዎች ከወትሮው ለየተ ባለ ማልያ ወደ ሜዳ ሲገቡ በጨዋታው ጅማሮ የመጀመሪያው ደቂቃዎች ላይ በቀኝ መስመር ሽመክት ጉግሳ ለሙጂብ ቃሲም አቀብሎት በሰበታ ከተማ ተከላካዮች ባወጡት አስደንጋጭ ሙከራ ጀምረዋል ::
ፋሲል ከነማዎች በተደጋጋሚ በቀኝ መስመር በሽመክት ጉግሳ በሚደረጉ የማጥቃት እንቅስቃሴዎች እድል ሲፈጥሩ ሲስተዋል ሰበታ ከተማዎች በመጀመሪያ የማጥቃት እንቅስቃሴያቸው በግራ መስመር ሀይለ ሚካኤል ያሻማውን ኳስ ተሞክሮ የግቡ አግዳሚ የመለሰውን ኳስ ፍፁም ገ/ማርያም አግኝቷት ሰበታን መሪ ያደረገች ጎል አስቆጥሯል ::
- ማሰታውቂያ -
ከጎሏ መቆጠር በኋላ ወደ ኋላ አፈግፍገው መጫወትን የመረጡት ሰበታዎች በሱራፌል ዳኛቸው እና በሽመክት ጉግሳ ተደጋጋሚ ሙከራዎች እንዲሁም እድሎችን መፍጠር ሲችሉ ተስተውሏል ::
ተደጋጋሚ ሙከራ ማድረጋቸው የቀጠሉት ፋሲሎች በሽመክት ጉግሳ አማካኝነት በቀኝ መስመር ያሻማው እና በዛብህ መለዮ ሞክሯት የሰበታ ተከላካይ ያወጣት መኩራ የምታስቆጭ አጋጣሚ ነበረች ::
በሰበታ በኩል በጨዋታ ወቅት ጉዳት ያጋጠመው የሰበታው አሊ ባድራ በ 35ኛው ደቂቃ በታደለ መንገሻ ተቀይሮ ሊወጣ ተገዷል ::
የመጀመሪያው አጋማሽ መጠናቀቂያ ላይ ፋሲል ከተማዎች ጎል አስቆጥረው በእለቱ የመሀል ዳኛ መሻሩን ተከትሎ በደጋፊዎች እና በፋሲል ተጫዋቾች መካከል ትልቅ ውዝግብን አስከትሎ የመጀመሪያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ ችሏል ::
ከመጀመሪያው አጋማሽ በተሻለ መልኩ የጎል ሙከራዎች የታዩበት እና ለተመልካኝች አዝናኝ በነበረው የሁለተኛ አጋማሽ ፋሲል ከነማዎች በ 46ኛው ደቂቃ ላይ ኦሴ ማውሊ የግል ብቃቱን በመጠቀም ፋሲልን አቻ ያደረገችውን ጎል ማስቆጠር ችሏል ::
ከጎሉ መቆጠር በኋላ ይበልጥኑ የተነቃቁት ፋሲል ከነማዎች ወደ ጎል ቶሎ ቶሎ ሲደርሱ ተስተውሏል :: ይህንንም ተከትሎ ከመሀል ሜዳ ሱራፌል ዳኛቸው ይዞት የገባውን ኳስ የሰበታ ከተማ ተጫዋቾች ጥፋት መስራታቸውን ተከትሎ የተሰጠው ቅጣት ምት ሱራፌል መቶት ግብ ጠባቂው ሲመልስ በእለቱ ጥሩ እንቅስቃሴን ሲያደርግ የቆየው ሽመክት ጉግሳ በደቂቃዎች ልዩነት ፋሲልን መሪ ያደረገች ጎል አስቆጥሯል ::
ከጎሉ መቆጠር በኋላ ሰበታ ከተማዎች ተጭነው ለመጫወት ቢሞክሩም የተሳካ ሙከራ ማድረግ ሳይችሉ ቀርተዋል ::
ፋሲል ከነማዎች በመጀመሪያ አጋማሽ ክፍተት ይታይበት በነበረው የግራ መስመር ላይ በሁለተኛው አጋማሽ ተሽለው በመግባት በመልሶ ማጥቃት ኦሴ ማውሊ ለሽመክት በረጅሙ አሻግሮለት ሸመክት ለሙጂብ ቃሲም ሳጥን ውስጥ አቀብሎት ሳይጠቀምበት የቀረው ኳስ የምታስቆጭ አጋጣሚ ነበረች ::
በጨዋታው ጥሩ እንቅስቃሴን ሲያደርግ የነበረው ሱራፌል ዳኛቸው በረጅሙ ለሙጂብ የሰጠውን ኳስ ሙጂብ በጥሩ አጨራረስ ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ በሊጉ ከሜዳው ውጪ ያስቆጠረው የመጀመሪያ ጎሉ ሆኖ ተመዝግባለታለች ::
ከጎሉ መቆጠር በኋላ ወደ ጨዋታ ለመመለስ የሞከሩት ሰበታዎች በፍፁም ገ/ማርያም የጭንቅላት ኳስ ጥሩ ሙከራ ቢያደርጉም በጎሉ የላይኛው አግዳሚ ታካ ወጥታለች ::
አጥቅተው መጫወት ብቸኛ አማራጫቸው የሆነው ሰበታዎች በሀይሉ አሰፋ ( ቱሳ ) እና ኢብራሂም ከድርን ቀይረው ማስገባት ችለዋል ::
ከተጫዋች ቅያሪ በኋላ የተሻለ ወደ ግብ መድረስ የቻሉት ሰበታዎች በቀኝ መስመር በኩል በበሀይሉ አሰፋ ሙከራዎችን ሲያደርጉ ታይተውል ::
የጨዋታውን ሙሉ ሰአት መጠናቀቀ ተከትሎ የእለቱ አራተኛ ዳኛ አራት ደቂቃዎችን ሲያሳዩ በጨዋታው መገባደጃ ላይ የተዘናጉት ፋሲል ከተማዎች ሁለት ጎሎችን ሊያስተናግዱ ችለዋል ::
በቀኝ መስመር በኩል በበሀይሉ አስፋ ቱሳ ያሻገረውን ኳስ ፍፁም ገ/ማርያም በእለቱ ሁለተኛውን ጎል ሲያስቆጥር ከደቂቃዎች በኋላም በፋሲል ተጫዋቾች መዘናጋት ከቀኝ መስመር የተሻማውን ኳስ የፋሲል ከነማውን ግብ ጠባቂ ሚኬል ሳማኪን ስህተት ተከትሎ አስቻለው ግርማ የአቻነቷን ጎል አስቆጥሯል ::
ውጤቱን ተከትሎ ፋሲል ከነማዎች የሊጉ መሪ መሆን የሚችሉበትን እድል ሲያባክኑ ሰበታ ከተማ አንድ ደረጃን በማሽሻል በአስራ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል ::