በአዞዎቹ አማካኝነት የመጀመሪያው የጨዋታው ክፍለ ጊዜ የተጀመረ ሲሆን ባለሜዳወቹ አርባምንጮች የመጀመሪያወቹን 15 ደቂቃዎች ተጭነው በመጫወት ወደ ተጋጣሚው ግብ ክልል መድረስ ሲችሉ በ10ደቂቃ ብርሀኑ አዳሙ እንዲሁም በ15ደቂቃ ምንተስኖት አበራ ጎል መሆን የሚችሉ ኳሶችን በማባከን አርባምንጭ ከተማን በጎል ቀዳሚ የሚሆንበትን እድል እዳይጠቀም አድርገውታል፡፡
16 ደቂቃ ላይ አባጅፍሮች በኦኪኪ አፎላቢ አማካኝነት ከበረኛ ጋር ተገናኝቶ ጎል የሚሆን ኳስ ከአግዳሚ ብረቱ በላይ በመምታት ወደ ውጭ የላካት ኳስ ለእንግዳወቹ ጅማወች የመጀመሪያ ሙከራ ነበረች፡፡
በመልሶ ማጥቃት ሲጫወቱ የነበሩት አርባምንጮች በ22ኛው ደቂቃ ጎልን ከመረብ ማገናኝት ሲችሉ እንዳለ ከበደ ከማእዘን ያሻማውን ኳስ በጥሩ ቦታ ላይ የነበረው ታዳጊው ተስፈኛ ብርሀኑ አዳሙ ወደ ግብ በመቀየር ደጋፊውን ማስደሰት ችሏል፡፡
ከዚች ግብ በሃላ በጥቂቱ የተነቃቁት አርባምንጭ ከተማወች በ30ደቂቃ ዮናታን ከበደ ወደ ግብ ከሞከራት ሙከራ ውጪ ወደ ሗላ በማፈግፈግ ሲከላከሉ ታይተዋል፡፡
የአርባምንጭን መከላከል ተከትሎ አንግዳዎቹ ጅማዎች በሔኖክ ና በዮናስ ገረመው አማካኝነት ካስን በማደራጀት መጫወት ሲችሉ በ38 ደቂቃ በአንድ ሁለት ቅብብል ወደ ጎል ደርሰው በዮናስ ገረመው አማካኝነት ጎል ማግባት ቢችሉም የመስመር ዳኛው ከጫዋታ ውጪ በማለት ሽሮባቸዋል፡፡ከዚህም ሙከራ በሗላ አርባምንጮች በመከላከል የመጀመሪያውን አጋማሽ 1-0 በሆነ ውጤት ነጥባቸውን አስጠብቀው መውጣት ችለዋል፡፡
- ማሰታውቂያ -
ድራማዊ የኳስ ትይንት በታየበት የሁለተኛው አጋማሽ ባለሜዳወቹ አርባምንጮች ተዳክመው የታዩበት እንዲሁም ተጋባዡ ጅማ አባጅፋር በኳስም ሆነ በሜዳ ላይ እንቅስቃሴ በልጠው የታዩበት ሆኗል፡፡
አባጅፍሮች የአዞዎቹን ደካማ ጎን በማጤን ወደ ሜዳ የገቡ ሲሆን በተደጋጋሚ በሔኖክ ና ዮናስ ገረመው ኳሶች ወደ ግብ ቢሞክሩም ኳሷ በበረኛው በመያዝ ና ወደ ውጪ በመውጣት አቻ መሆን ተስኗቸው ቆይተዏል፡፡ በአርባምንጭ በኩል ሙሉ የሁለተኛ አጋማሽ ክፍለ ጊዜውን በመከላከል ማሳለፉን ተከትሎ ጅማዎች በሜዳቸው የሚጫወቱ ነበር ሚመስለው፡፡
የአሰልጣኝ ፀጋዬ ኪ/ማርያም የተጫዏቾች ቅያሬ የመከላከል ታክቲካቸውን በማዳከም የጎሏ ሚናውን ተጫውቷል፡፡ በዚህም መሰረት በ70ደቂቃ ከዮናስ ገረመው የተላከለትን ኳስ አጥቂው ኦኪኪ አፎላቢ በሚገርም ሁኔታ ወደ ግብ በመቀየር አባጅፋሮችን አቻ ማድረግ ችሏል፡፡
ከዚህችም ጎል መቆጠር በሗላ በሜዳው ሚገኝው ደጋፊ አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪ/ማርያምን በመቃወም የተቃውሞ ድምፅ ያሰሙ ሲሆን መረጋጋት ያልቻሉት አርባምንጮች በ75ደቂቃ ላይ በተከላካዩ ተመስገን ካስትሮ የተሰራውን ጥፍት ባግባቡ በመጠቀም አኪኪ አፎላቢ ወደ ግብ በመቀየር ጅማዎችን ወደ 2-1 መሪነት ከፍ ማድረግ ችሏል፡፡
ቀኑ የስራ ቀን ቢሆንም ውጤት ፈላጊው የአርባምንጭ ደጋፊ በሜዳው በመገኝት ጨዋታውን ቢከታተልም በክለብ አቋም መውረድ ከፊሉ ደጋፊ ሜዳውን ለቆ ወጥቷል፡፡
የፀጋዬ ኪ/ማርያም ያልተገባ የተጨዋች ቅያሪ በታየበት ጨዋታ አርባምንጭ ከተማወች ወደ ተቃራኒ ግብ ክልል በመድረስ የአቻ ግብ ሚሆን ኳስ መፍጠር ቢችሉም የጅማ ተከላካዮችን ማለፍ ተስኗቸው ግብ ማግባት ሳችሉ ቀርተዋል፡፡ ከ2-1 ውጤት በሃላ በመልሶ ማጥቃት ስጫወቱ የነበሩት ጅማወች በ90 ደቂቃ ከዮናስ ገረመው በመስመር የተሻማውን ኳስ የጨወታው ኮከብ የነበረው አኮኪ አፎላቢ በግሩም ሁኔታ በማስቆጠር ለራሱ ና ለክለቡ 3 ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ መስራት ችሏል፡፡ ከግቧ መቆጠር በሃሏ የአርባምንጭ ደጋፊዎች ለተጫዋቹ ያላቸውን አድናቆት ቆመው በማጨብጨብ ገልፀዋል፡፡ጨዋታውም በጅማ አባጅፋር 3-1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
አርባምንጭ ከተማ መሸነፉን ተከትሎ ወራጅ ቀጠናውን ሲቀላቀል አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪ/ማርያም ከአሰልጣኝነት ሊሰናበቱ እንደሚችሉ ይጠበቃል፡፡
የአሰልጣኞች አስተያየት
ገብረመድህን ሀይሌ -ጅማ አባጅፋር
“ባሳለፍነው ሳምኔት ኢትዮጵያ ቡናን በሜዳችን ማሸነፋችን ተከትሎ በስነ ልቦና ጠንካራ እንድንሆን እረድቶናል፡፡ በዛሬው ጨዋታ ጎል ከተቆጠረብን በኃላ አጥቅተን በመጫወታችን አሸነፊ ልንሇን ችለናል፡፡የፊት አጥቂያችን ኦኪኪ አፎላቢ ሀትሪክ በመስራቱ አድናቆት እሚቸረው ነው”
አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪ/ማሪያም ድህረ ጨዋታ አሰተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡