በዘጠነኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከተደረጉት ጨዋታዎች መካከል በባህርዳር አለማቀፍ ስታዲዮም የተደረገው የባህርዳር ከተማ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲ ጨዋታ በባለሜዳዎቹ 3-2 አሸናፊነት ተጠናቋል።
ባህር ዳሮች በሲዳማ ከተሸነፉበት ስብስብ ፍቃዱ ወርቁ እና ደረጀ መንግስቱን በማሳረፍ ከጉዳት መልስ ፍፁም አለሙን እና ዜናው ፈረደን በመጀመሪያው አሰላለፍ ሲያካትቱ እንግዳው ክለብ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቱ በበኩሉ በሀድያ ሆሳዕና ከተሸነፈበት ስብስብ ውስጥ ጃፋር ደሊል፣ሰመረ ሀብተይ እና ራምኬል ሎክን በአብዱላዙዝ ኬታ፣ብሩክ ሰሙ እና አሞስ አቼምባግ ቀይረው ወደ ሜዳ ገብተዋል
- ማሰታውቂያ -
ትናንት በህመም ምክንያት ህይወቱ ላለፈው የባህር ዳር ከነማ ደጋፊ የህሊና ፀሎት በማድረግ የተጀመረው የሁለቱም ቡድኖች ጨዋታ። በመጀመሪያው አጋማሽ ሶስት ግቦች ተስተናግደውበታል።
ተቀራራቢ የሆነ የጨዋታ እንቅስቃሴ ይዘው ወደ ሜዳ የገቡት ሁለቱም ቡድኖች በተለይ የመጀመሪያዎቹ 10 ደቂቃዎች ረጃጅም ኳሶችን ሲጠቀሙ ተስተውሏል። በ 10ኛው ደቂቃ ማማዱ ሲዲቤ ላይ በተሰራው ጥፋት የተገኘው የቅጣት ምት
ግርማ ዲሳሳ በግምት ከ40 ሜትር ርቀት ያሻማውን ኳስ አንበሉ ፍቅረ ሚካኤል አለሙ በግንባር በመግጨት ግብ አስቆጥሮ ቡድኑን መሪ ማድረግ ችሏል። ከግቧ መቆጠር በኃላ ጫና ፈጥረው መጫዎት የቻሉት ባለሜዳዎች 20ኛው ደቂቃ ላይ ዜናው ፈረደ ሁለተኛ ግብ ቢያስቆጥርም ከጨዋታ ውጭ ተብሎ ተሾሮበታል። በጨዋታው ጥሩ የነበሩት ባህርዳሮች ተጫዋቾቻቸው የሚሰሯቸው ስህተቶች ግን ዋጋ ሲያስከፍሏቸው ተስተውሏል። በዚህም ምክንያት በ23ኛው ደቂቃ አቻምፖንግ አሞስ ከተጫዋቾች እግር ስር ነጥቆ ያሻገረለትን ኳስ ተጠቅሞ ናሚቢያዊው አጥቂ ኢታሙኒ ኬሙኒ የአቻነት ጎል ማስቆጠር ችሏል ። ግብ ቢቆጠርባቸውም በድጋሚ መሪነታቸውን በእጃቸው ለማስገባት ሲታትሩ የነበሩት ባለሜዳዎቹ። በ26ኛው ደቂቃ ላይ ማሀመድ ሲዲቤ በቅርብ ርቀት የገጨውን ኳስ ግብ ጠባቂው አብዱልአዚዝ ከይታ ያዳነበት የሚያስቆጭ አጋጣሚ ነበር።
ውልዋሎዎች በበኩላቸው ብሩክ ለማ አማካኝነት የባህርዳርን ተከላካይ ክፍል በተደጋጋሚ ሲረብሽ ተስተውሏል ። በ32ኛው ደቂቃ ግርማ ዲሳሳ ሳጥኑ ጠርዝ ላይ ሆኖ የመታትን ኳስ በማስቆጠር ባህርዳሮችን በድጋሚ መሪ ማድረግ ችሏል። በሁለቱም ቡድኖች በኩል ተጨማሪ ግቦችን ለማስቆጠር ከፍተኛ ጥረት ቢደረግም ተጨማሪ ግቦች ሳይታከሉ በባለሜዳዎቹ 2-1 መሪነት ለእረፍት ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል።
በብዙ ውዝግቦች ታጅቦ የተከናወነው ሁለተኛው አጋማሽ። 49 ደቂቃ ላይ በብሩክ ለማ አማካኝነት ያከናወኑት ሙከራ ጥቃት መስንዘር የጅመሩት ወልዋሎዎች። ከሶስት ደቂቃዎች በኋላም ጁሊያን ናያንጂቡ የመታውን ኳስ አዳማ ሲሴኮ ለጥቂት አውጦበታል። ተመጣጣኝ ፉክክር የታየበት ሁለተኛው አጋማሽ። 65ኛው ደቂቃ ላይ ብሩክ ለማ ግብ አስቆጥሮ እንግዳዎችን በድጋሚ አቻ ቢያደርግም። በ68ኛው ደቂቃ ግርማ ዲሳሳ ከግራ ጠርዝ ያሻማውን ኳስ ሳሙኤል ዩሃንስ በራሱ መረብ ላይ በማሳረፍ ባህርዳሮችን በድጋሚ መሪ እንዲሆኑ አድርጓል። ከጎሏ መቆጠር በኃላ ወልዋሎዎች የተጎዳ ተጫዋች እያከመ የነበረው ወጌሻ ሜዳ ሳይወጣ ነው ጨዋታው ተጀምሮ ግቡ የተቆጠረብን በማለት ጨዋታው ለ 13 ደቂቃ ያክል ተቋርጦ ቆይቷል።
ጨዋታው እንደገና ቢጀምርም በፊሽካ እና በተጫዋቾች ጉዳት ይቆራረጥ ስለነበር ጨዋታው አሰልቺ እንዲሆን አድርጎታል። ሆኖም ግን ቢጫ ለባሾቾ በጨዋታው መገባደጃ ሳይጠቀሙበት የቀሩት የሀሪትሰን ሄሱ ስህተት እጅግ በጣም አሰቆጪ ነበር ። በቀሪዎቹ ደቂቃዎች ግብ ሳይሰተናገዱበት በባለሜዳዎቹ ባህርዳሮች 3-2 አሸናፊነት ተጠናቋል።