በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 5ኛ ሳምንት ጨዋታዎች መካከል 6ቱ ዛሬ የተደረጉ ሲሆን ከነዚህ ጨዋታዎች መካከል ኢትዮጵያ ቡና ከድሬዳዋ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ አንዱ ነው። ይህን ጨዋታ እንደሚከተለው ዳሰነዋል።
9:00 ላይ ድሬደዋ ላይ ድሬደዋ ከተማ ኢትዮጵያ ቡናን ያስተናገደበት ጨዋታ ያለግብ አቻ ተጠናቋል። በሊጉ እጅግ ደካማ ጉዞ ላይ የነበረው ድሬዳዋ ከተማ እና በሊጉ እጅግ በጣም መሻሻል እያሳየ የነበረው ኢትዮጵያ ቡና ያደረጉት ጨዋታ እንደተጠበቀው ሳይሆን ያለግብ ተጠናቋል። በሊጉ ድሬደዋ ከተማ በርካታ ግብ የተቆጠረበት ክለብ ሲሆን ኢትዮጵያ ቡና ደግሞ እየተሻሻለ መምጣቱ ግብ ያስተናግዳል ተብሎ ተጠብቆ ነበር። ሆኖም የረባ እንኳን እንቅስቃሴ ሳይደረግበት ተጠናቋል።
- ማሰታውቂያ -
በጨዋታው 9ኛ ደቂቃ ላይ ድሬደዋ ከተማ ወደግብ በመድረስ ግብ ያስቆጠሩ ቢሆንም ከጨዋታ ውጪ ተብሎ ተሽሮባቸዋል። ምንም የሚስብ ጨዋታ ያልተስዋለበት ጨዋታ የተሻለ ሙከራ ሳይደረግበት የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቋል። ሁለተኛው አጋማሽም ድሬደዋ ከተማ ወደ ኋላ አፈግፍገው ሲጫወቱ ኢትዮጵያ ቡና በተቃራኒው ጫና ፈጥረው ለመጫወት ሞክረዋል። ሆኖም ግን ሙከራቸው ፍሬ ማፍራት ሳይችል ቀርቷል። በኢትዮጵያ ቡና በኩል ሊጠቀስ የሚችለው 85ኛው ደቂቃ ላይ አጥቂው አቡበከር ነስሩ ያደረገው ሙከራ ነው። ከዚህ በኋላም የረባ ሙከራ ሳይደረግ ጨዋታው ያለግብ ተጠናቋል። ውጤቱንም ተከትሎ ኢትዮጵያ ቡና በ6ነጥቦች 9ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ድሬደዋ ከተማ ደግሞ ከኢትዮጵያ ቡና በ2ነጥቦች ዝቅ ብሎ በ4ነጥቦች 15ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ሊጉን አንድ ጨዋታ የሚቀረው ወልዋሎ አ.ዩ. በ10 ነጥቦች ሲመራ ሲዳማ ቡና በ9 እንዲሁም ባህርዳር ከተማ በ8ነጥቦች ተከታዮቹን ደረጃ ይዘዋል። የኮከብ ጎል አግቢነቱን ደግሞ የፋሲል ከተማው ሙጂብ ቃሲም፣ የኢትዮጵያ ቡናው እንዳለ ደባልቄ፣ የባህርዳር ከተማዎቹ ማማዱ ሲዲቤ እና ፍፁም ዓለሙ እንዲሁም የሀዋሳ ከተማው ብሩክ በየነ በእኩል 4 ግቦች ሲመሩ አዲስ ግደይ፣ ዳዋ ሁቴሳ፣ አማኑኤል ገ/ሚካኤል፣ ይገዙ ቦጋለ እና ሰመረ ሀፍተይ በእኩል 3ግቦች ተከታዩን ደረጃ ይዘዋል።