በ 6ተኛው ሳምንት ቅዳሜ በተደረገ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የወንድማማቾች ደርቢ ጨዋታ ጎንደር ላይ ፋሲል ከነማ ባህር ዳር ከነማን አስተናግዶ ሶስት ለባዶ ማሸነፋ ችሏል።ባለ ሜዳዎቹ አፄዎቹ ወደ ሰበታ አቅንቶ ባለቀ ሰዐት በተቆጠሩበት 2 ግቦች አቻ ወጥቶ ከተመለሰው ስብስባቸው ምንም ለውጥ ሳያደርጉ ነበር ወደ ሜዳ የገቡት፡፡
ከአፄዎቹ የደጋፊ ማህበር
ለቀድሞ ተጨዋቻቸው ፍፁም ከበደ የክብር
ስጦታ በመስጠት የተጀመረው እና በውብ የደጋፊዎች ዝማሬ ና የስታዲየም ድባብ የጀመረው ጨዋታ በመጀመሪያ አጋማሽ ብዙም ሳቢ ባልሆነው እና ተደጋጋሚ ፍውሎች የተስተዋሉበት የመጀመሪያዎቹ ደቂቃዎች ሽመክት ላይ በተሰራ ጥፋት የተገኘውን ቅጣት ምት ሱራፌል በግሩም ሁኔታ የሞከረበት አጋጣሚ የመጀመሪያ ሙከራ ነበረች፡፡በዚህም አጋጣሚ የተገኘችውን የማእዘን ምት እራሱ ሱራፌል ያሻማዉን ኳስ በእለቱ በአሪፍ ሲንቀሳቀስ የነበረው ኦሲ ማውሊ በግንባሩ በመግጨት ባለ ሜዳዎቹ መሪ እንዲሆኑ ያደረገችውን ኳስ መረብ ላይ አሳርፏል፡፡ከጎሉዋ መቆጠር በኋላ ተመጣጣኝ በሆነ የ ኳስ ፍሰት የተሻለ ሙከራ ማድረግ ቢችሉም የመጀመሪያው አጋማሽ በፋሲል መሪነት ተጠናቁዋል፡፡
- ማሰታውቂያ -
በሁለተኛው አጋማሽ የተሻለ የኳስ እንቅስቃሴ ቢታይም በባህርዳር ከነማዎች በኩል ረጃጅም ኳሶችን ለመጫወት ሞክረዋል።ሆኖም የፋሲል ከነማ ተከላካዮች በጭራሽ ሊቀመሱ አልቻሉም፡፡በነ ሽመክት ጉግሳና ሱራፌል ዳኛቸው በተደጋጋሚ የተቃራኒ ቡድን ሜዳ በመድረስ የጨዋታውን ሁኔታ ለመቀየር ሲሞክሩ ተመልክተናል፡፡ብዙ ውጥረቶች በታዩበት የሁለተኛው አጋማሽ በዛብህ መለዮ በግሩም ሁኔታ ያሻማውን ኳስ የጭዋታው ኮኮብ የነበረው ኦሲ ማውሊ በድጋሚ በግንባሩ በመግጨት ባህርዳር ከነማ መረብ ላይ አሳርፏል።በመጨረሻም ጨዋታው ሊጠናቀቅ ሲል ልማደኛው የጎል አዳኝና የኢትዮጵያ ፕሪሜር ሊግ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ሙጅብ ቃሲም ጎል በማስቆጠር ጨዋታው በፋሲል ከነማ 3-0 እንዲጠናቀቅ አድርጉዋል፡፡
በጨዋታው መጨረሻ ደቂቃ ላይ በበዛብህ መለዮ ተቀይሮ የገባው የፋሲል ከነማው ወጣት ተጫዋች ኤፍሬም ክፍሌ ምናልባትም ወደ ፊት የኢትዮጵያ እግር ኳስን ይቆጣጠራሉ ተብለው ተስፋ ከተጣለባቸው ወጣት ተጫዋቾች አንዱ እንደሚሆን ከዚህ በፊት ባሳየን የውስጥ ውድድሮች ተመልክተነዋል ፡፡
ውጤቱን ተከትሎ ፋሲል ከነማ ነጥቡን ወደ 11 በማሳደግ የሊጉ መሆን ሲችሉ በአንፃሩ እንግዳው ቡድን ባህርዳር ከነማ 8 ነጥብ በመያዝ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡