ሰርጆቪች ሚቾ በይፋ የዛምቢያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ።
ሚቾ የዛምቢያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ለመሆን የመጨረሻ ሶስት እጮች ላይ በመካተት ከጫፍ መድረሳቸው ከሳምንታት በፊት መዘገባችን ይታወሳል :: ዛሬ የወጡት መረጃ ደግሞ ሰርጆቪች ሚቾ ዛሬ በይፋ ብሄራዊ ቡድኑን መረከባቸው አሳውቀዋል ። አሰልጣኙ በሚቀጥለው ሳምንት ወደ ዛምቢያ በመብረር በሁለት አመት ውል ፊርማቸውን እንደሚያኖሩ ይጠበቃል። በአፍሪካ ሊጎች ከፍተኛ እውቀት ያላቸው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከዛምቢያ ብሄራዊ ቡድን ጋር ጥሩ ስኬትን ያመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከዚህ ቀደም የዩጋንዳ ብሄራዊ ቡድንን በመያዝ በአፍሪካ ዋንጫ መሳተፋቸው አይዘነጋም።