ህዳር 14 ቀን የተቋቋመው አስመራጭ ኮሚቴ በትናንትናው ዕለት የብዙሃኑን የሚዲያ እካላት ጥያቄ ያልመለሰ የይስሙላ ጋዜጣዊ መግለጫ በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል መስጠቱ ይታወሳል።
በርካታ የህግ ጥሰቶችን ፈፅሞ በሚዲያዎች ፊት የቀረበው አስመራጭ ኮሚቴው ከሚዲያ አካላት ለቀረቡት በርካታ ኮርኳሪና አንገብጋቢ የህዝብ ጥያቄዎች በመድረኩ መሪዎች አቅም ማነስና ሽፋፋኝነት በቂና አሳማኝ ምላሽ ሳያገኝ ነው ይተጠናቀቀው።
በበርካታ የህግ ጥሰቶችና ህፀፆች የተሞላው አስመራጭ ኮሚቴው ሠመራ ላይ ይካሄዳል ተብሎ ለሚጠበቀው ምርጫ 5 ለፕሬዝዳንታዊ 16 ደግሞ ለስራ አስፈፃሚነት የሚወዳደሩ ዕጩዎችን ማንነት ቢያሳውቅም ጠቅላላ ጉባኤውና ምርጫው በተያዘለት ቀን ታህሳስ 16 ይካሄዳል?የሚለው ቁርጥ ያለ ምላሽ ሣያገኝ ቆይቷል።
ሀትሪክ ከደቂቃዎች በፊት ባገኘችው የተረጋገጠ መረጃ ሠመራ ላይ ታህሳስ 16 ቀን ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀው ምርጫ ወደ ጥር 5 ቀን መዘዋወሩ ተረጋግጧል።
ፊፋ ምርጫ ለማካሄድ የያዛችሁት ቀን ታህሳስ 16 ቀን የፈረንጆች ገና የሚከበርበት በመሆኑ በጉባኤው ለመሳተፍ ስለምቸገር ምርጫችሁን ለ10 ቀናት እራዝሙ በማለት ደብዳቤ የላከ ሲሆን አስመራጭ ኮሚቴው በበኩሉ ፈረንጆች ገና ስንል አራዝመን የእኛስ?የሚል ጥያቄን በማስነሳቱ ምርጫው በ19 ተጨማሪ ቀናቶች ተራዝሞ ጥር 5 ቀን ሠመራ ላይ እንዲካሄድ አስመራጭ ኮሚቴው ያለ ልዩነት በሙሉ ድምፅ ወስኗል።ይሄንን ውሳኔ ተከትሎ በግርግሩ መሹለክ የፈለጉ ዕጩ ተወዳዳሪዎችና የስልጣን ጀምበራቸው የጠለቀችባቸው የግለሰብ አጀንዳን የሚያራምዱ የቀድሞ ስራ አስፈፃሚዎች እንዴት ይራዘማል? በሚል አስመራጭ ኮሚቴው ላይ የተለያዩ ጫናዎችን እያደረጉ ቢሆንም አስመራጭ ኮሚቴው ምርጫው ለ ጥር 5 መራዘሙን ለፈፋ አሳውቆ ፊፋም ውሳኔውን ስለመቀበሉና በምርጫው ዕለት ታዛቢ እንደሚልክ ማረጋገጫ መላኩም ታውቋል።
ሰበር ዜና፡-ሰመራ ላይ ታህሳስ 16 ይካሄዳል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ጠ/ጉባኤና ምርጫ ጥር 5 እንዲካሄድ አስመራጭ ኮሚቴው ወሰነ
![](https://i0.wp.com/www.hatricksport.net/wp-content/uploads/2017/11/4cWuI15O8BpBJsFvbPLhnuMS7JCsd2XRGVz6XCiDejvGDAgKTZs8G3jQy4hfupFJ0X0FGzhPg1LDlvNSHtiDGzx6i3zEKH-Aj15OzVsV8dUAzpR2F6FxHCwVP94OjJ6hRYy6FzeKQLCI8j5-HNfEfXwDDJo7rgHCg9kkKVBaDNT9w320-h274-nc.jpeg?resize=320%2C274&ssl=1)
Hat-trick Weekly Sport Newspaper Founder & Managing Editor.
The First Color Sport Newspaper in the country.