በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመሩት ሰበታ ከተማዎች ወደ ዝውውሩ የተጫዋቾቻውን ውል በማራዘም እና አዳዲስ ተጫዋቾችን በመቀላቀል የጀመሩት ሰበታዎች በዛሬው ዕለት መሳይ ፓውሎስን ማስፈረማቸው ተገልጿል ።
ሰበታ ከተማ በሐዋሳ ከተማ ድንቅ የሚባል የውድድር ዓመትን በተከላካይ ስፍራ ላይ ያሳለፈውን መሳይ ፓውሎስን ወደ ቡድናቸው ሲቀላቅሉ ሊጉ ዳግም ሲካሄድ ከአዲስ ተስፋዬ እና አንተነህ ተስፋዬ ጋር የሚያሳየው ብቃት ይጠበቃል ።
መሳይ ፓውሎስ በዘንድሮው የውድድር ዓመት በሐዋሳ ከተማ ቤት በመከላከሉ ረገድ ለቡድኑ የተሻለውን አድርጎ ሲታይ ቡድንን የሚመራበት መንገድም ተጫዋቹን በዘንድሮው የውድድር ዓመት ጎልቶ እንዲታይ አድርጎታል ።