ሳምንታዊ ባለቀለም የስፖርት ጋዜጣ የሆነችው ተወዳጇ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ እንደተለመደው ሁሉ ነገም ማክሰኞ ጥር 15/2010 ዓ.ም በማለዳው ከእጅዎ ልትገባ መሰናዶዋን አጠናቅቃለች፡፡
ለመሆኑ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ይሆን?
-ከሀገር ውስጥ፡- የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ጁነዲን ሀገራችን የቻን አፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅነት ባንዲራን ከሞሮኮ ለመረከብ ወደ ስፍራው ስለሚጓዙበት ሁኔታ መረጃ የቀረበላችሁ ሲሆን፤ ሌላው የቅዱስ ጊዮርጊስ የአማካይ ክፍልን በክረምቱ ወራት የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት የተቀላቀለውና ለክለቡም በጉዳት ሳቢያ እስከአሁን ድረስ መጫወት ያልቻለው ተደናቂው የአማካይ ስፍራ ተጨዋች ታደለ መንገሻ ወደ ህንድ ተጉዞ ህክምናውን ካደረገ በኋላ በቅርቡ ወደ ሜዳ ሊመለስ መሆኑን ተከትሎ ተጨዋቹ ከሀትሪክ ስፖርት ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ቆይታ አድርጓል፤ ከእዚያ ውጪም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን አስመልክተን በሊጉ የአሁን ሰዓት የውድድር ተሳትፎው ላይ ጥሩ ውጤት እያስመዘገቡ ከሚገኙት ክለቦች መካከል ለመቀሌ ከተማ በመሀል ሜዳ እየተጫወተ ከሚገኘው ታታሪው ተጨዋች አመለ ሚሊኪያስ ጋር ያደረግነውም ቆይታ አለን፡፡
ከባህር ማዶ፡- ብራዚላዊው የኳስ ምትሃተኛ ሮናልዲኒሆ ጎቾ ሲታወስ በሚል የቀረበ ጣፋጭ ዘገባ ያለላችሁ ሲሆን የአርሰናሉ አሌክሲስ ሳንቼዝም በመጨረሻ የማንቸስተር ዩናይትድ ንብረት መሆኑን ተከትሎ ሰፊ ዘገባ ቀርቧል፤ ሳንቼዝ ወደ ማን. ዩናይትድ መዘዋወሩን ተከትሎም 600 ሺ ፓውንድ ደመወዝ የሚከፈለው ሲሆን ታሪካዊውን 7 ቁጥር ማሊያም በክለቡ ቆይታው ይለብሳል፡፡
የአርሰናሉ ጃክ ዊልሼርም ከኦዚል ጋር መጫወት እግር ኳስን ያቀላል በሚል ሀሳቡን ሰጥቷል፡፡ ሌላው የሀትሪክ ስፖርት የነገው ዘገባችን ሜኪታሪያን በማንቸስተር ዩናይትድ ለምን አልተሳካለትም፤ ለአርሰናልስ ምን ይዞለት ይመጣል በሚለው ሀሳብ ዙሪያም ሰፊ ዳሰሳ ሊቀርብ ችሏል፤ ከእዚያ ውጪ ሌሎች አስተያየቶችና ዜናዎችም ሊቀርብላችሁ በቅቷል፡፡
በኦልዲስ በት ጉዲስ አምዳችን ደግሞ “እርሻ ሰብል በቀድሞ ጊዜ ለታላላቅ ክለቦች ፈተና እንደነበረና በጥሩ ብቃቱም በክለቡ ውስጥ ተጫውቶ ማለፉን የቀድሞ የቡድኑ የአማካይ ስፍራ ስኬታማ ተጨዋች ብስራት ጌታቸው አስተያየቱን ሰጥቷል፤ ብስራት በእዚህ ዓምድ ቆይታው ለቀድሞ የቅዱስ ጊዮርጊስ አጥቂ ሙሉጌታ ከበደ ባለው ጥልቅ ፍቅር እንደ እሱ ሀሉ 2 ቁጥርን ለብሶ መጫወቱንም በዘገባው ይተርክልናልና ጋዜጣው እንዳያመልጦት።
እናም ሌሎች ያልተሰሙ አዳዲስና ትኩስ ዘገባዎችን ነገ ማለዳ ይዛ እጅዎ ትገባለች፡፡
በርካታ አንባቢዎቻችን ባቀረባችሁልን ተደጋጋሚ ጥያቄ መሰረት ሀትሪክን በሳምንት ሁለት ቀን በቅርቡ ይዘን እንቀርባለንና ጠብቁን፡፡ ተጨማሪና ትኩስ መረጃዎችን በርካታ ተከታታዮች ባሉት hatricksport.com ድረ-ገፃችን ላይ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡
መልካም ንባብ
ሳምንታዊ ባለቀለም የስፖርት ጋዜጣ የሆነችው ተወዳጇ ሀትሪክ ስፖርት
![](https://i0.wp.com/www.hatricksport.net/wp-content/uploads/2018/01/FB_IMG_1516646080615.jpg?resize=552%2C801&ssl=1)
Editor at Hatricksport website