በስዊድን ሁለተኛ ሊግ በ14ኛው ሳምንት ከሜዳው ውጪ ትሬሌቦርግስን የገጠመው ስይሪያንስካ በአሕመድ እና ቢንያም ግቦች ታግዞ ማሸነፍ ችሏል።
ለእዲስ ክለቡ ስይሪያንስካ የመጀመሪያ ግቡን ማስቆጠር የቻለው ቢንያም በላይ ክለቡ ከወራጅነት ስጋት ለመውጣት በሚያደርገው ጥረት ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል።
- ማሰታውቂያ -
ከዚህ ቀደም ከሚታወቅበት የመስመር እጥቂነት በተለየ መልኩ የእጥቂ እማካይ ስፍራ ላይ እየተጫወተ ሚገኘው ቢንያም የክለቡ የማጥቃት እንቅስቃሴን እየመራ ይገኛል።
ውጤቱን ተከትሎ ስይሪያንስካ ነጥቡን 15 በማድረስ 12 ደረጃ ላይ ተቀምጧል።