በትናንትናው እለት የተጀመረው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ዙር የ16ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በዛሬው እለትም ቀጥሎ ተካሂዷል።
በፕሪምየር ሊጉ የ2ኛ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታዎችም ዛሬ 9 ሰዓት ላይ ሶስት ጨዋታዎች ተካሂደዋል።
አርባ ምንጭ ከተማ በሜዳው ላይ የሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስን ያስተናገደበት ጨዋታም ዛሬ በ9 ሰዓት ላይ ከተደረጉ ጨዋታዎች አንዱ ነው።
- ማሰታውቂያ -
በጨዋታውም ቅዱስ ጊዮርጊስ አርባንጭ ከተማን በሜዳው 4ለ1 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
በጨዋታው ላይ ለቅዱስ ጊዮርጊስ በሀይሉ ግርማ በ44ኛው ደቂቃ፣ አዳነ ግርማ በ65ኛው እና በ71ኛው ደቂቃ እንዲሁም ቡርኖ ኮኔ ጨዋታው ተጠናቆ በባከነ ሰዓት 1ኛ ደቂቃ አስቆጥረዋል። አርባ ምንጭ ከተማ በባዶ ከመውጣት የታደገችውን ጎል ደግሞ ታደለ መንገሻ በ92ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፏል።
በሌላ ጨዋታ በጎንደር ፋሲለደስ ስታዲየም ሲዳማ ቡናን ያስተናገደው ፋሲል ከነማ በሜዳው ተረትቷል።
በጨዋታው ሲዳማ ቡና በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ 3ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘውን ፋሲል ከነማን 3ለ1 በሆነ ውጤት መርታት ችሏል። በተመሳሳይ ኢትዮጵያ ቡና እና ደደቢት በአዲስ አበባ ስታዲየም ጨዋታቸውን አድርገዋል።
ጨዋታውም ያለ ምንም ግብ በአቻ ውጤት የተጠናቀቀ ሲሆን፥ ሁለቱ ክለቦች ሁለተኛ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን ነጥብ በመጋራት ጀምረዋል።
በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ደግሞ አዲስ አበባ ከተማ ሀሳዋ ከተማን ያስተናገደ ሲሆን፥ ጨዋታውም በሃዋሳ ከነማ 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸናፊነት ተጠናቋል። በጨዋታውም ጊት ጋትኮች በ69ኛው ደቂቃ ለሀዋሳ ከተማ የማሸነፊያዋን ብቸኛ ጎል ከመረብ አሳርፏል።
ዛሬ በ10 ሰዓት ድሬደዋ ላይ የተገናኙት ድሬ ደዋ ከተማ እና አዳማ ከተማ ደግሞ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል።
በትናንትናው እለት በተካሄዱ የ16ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎችም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከወልድያ ከተማ አቻ ተለያይቷል።
በሌላ ጨዋታም የኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ጅማ አባ ቡና ጨዋታ ያለምንም ግብ ተጠናቋል፡፡
# | ክለብ | ተጫ | ልዩ | ነጥብ |
---|---|---|---|---|
1 | ![]() |
16 | 19 | 32 |
2 | ደደቢት![]() |
16 | 9 | 28 |
3 | ![]() |
16 | 4 | 28 |
4 | ![]() |
16 | 4 | 27 |
5 | ![]() |
16 | 5 | 26 |
6 | ![]() |
16 | 3 | 25 |
7 | ![]() |
16 | 1 | 22 |
8 | ![]() |
16 | -1 | 21 |
9 | ![]() |
16 | 0 | 20 |
10 | ![]() |
16 | -5 | 18 |
11 | ![]() |
16 | -5 | 17 |
12 | ![]() |
16 | -2 | 16 |
13 | ![]() |
16 | -8 | 16 |
14 | ![]() |
16 | -5 | 14 |
15 | ![]() |
16 | -9 | 14 |
16 | ![]() |
16 | -9 | 10 |