8ተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዕለተ እሁድ ላይ ሰባት ጨዋታዎችን ያካሂዳል።በትግራይ ስታድየም ላይ ሚካሄደው የወልዋሎ ና ሀድያ ሆሳእና ጨዋታን ከጨዋታው በፊት በዚህ መልኩ ዳስሰነዋል።
ወልዋሎ አዲግራት ከ ሀድያ ሆሳእና
የጨዋታ ቀን: እሁድ ጥሪ 2/2012
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር: ኢንተርናሽናል አርቢትር ሊድያ ታፈሰ
ቦታ: ትግራይ ስታድየም
ባሳለፍነው ሳምንት ከተከታታይ ነጥብ ማጣት በኃላ ማሸነፍ የቻሉት ወልዋሎዎች መሪነታቸውን ለማስጠበቅ የሊጉ ጊርጌ ላይ ሚገኘውን ሀድያ ሆሳእናን ማሸነፍ ግድ ይለዋል።ባለፋት ጨዋታዎች ላይ ወሳኝ ተጨዋቾቹን በጉዳት ያጣው ወልዋሎ በነገው ጨዋታም በተመሳሳይ አይናለም ሀይሉ፣አሞስ አቼምፖንግ እና ካርሎስ ዳምጠውን ማያሰልፍ ይሆናል።
ድሬዳዋን ባሸነፋበት ጨዋታ ተፈጥሮአዊ የመሀል ሜዳ ተጨዋቾችን ይዘው የገቡት ቢጫ ለባሾቹ ነገም የተጋጣሚያቸውን የመሀል ሜዳ ጥንካሬ በግምት በማስገባት ተመሳሳይ አቀራረብ ይዘው ሊገቡ እንደሚችሉ ይገመታል።ፊት ላይ ጥሩ ጥምረት እየፈጠሩ ሚገኙት ናሚብያውያኑ ኢታሙና ኩሜይኒ ና ጁንያንስ ናጋንጂቦ ከሜዳው ውጪ ወደ ኃላ ሚያፈገፍገውን የሀድያን ተከላካይ ክፍል ማስከፈት ላይ ከባድ ስራ ይጠብቃቸዋል።በተለይ ቡድኑ ላይ ያለው የፈጣሪ ተጨዋች እጥረት አጥቂዎቹን ለተጨማሪ ጥረት ሲያጋልጣቸው ይታያል።
- ማሰታውቂያ -
የሊጉ የመጀመርያ ድላቸውን ሲዳማ ቡና ላይ ያስመዘገቡት ሀድያ ሆሳእናዎች የነገው ጨዋታ ከሜዳቸው ውጪ እንደመሆኑ ወደ ኃላ ተስበው ጥንቃቄ ላይ መሰረት ያደርገ አቀራረብን ይጠቀማሉ ተብሎ ይጠበቃል።አምስት ነጥቦችን ሰብስበው የሊጉ መጨረሻ ደረጃን ይዘው ሚገኙት ሀድያዎች ለነገው ጨዋታ የመሐመድ ናስርና ኢዮኤል ሳሙኤልን ግልጋሎትን በጉዳት ምክንያትማያገኙ ይሆናል።
3-5-2(ኳስ ሲነጠቁ ወደ 5-3-2 ሚቀየር) የጨዋታ ስልትን ተመራጭ ሚያደርጉት ሀድያዎች ከመስመር ና ከመሀል በሚንሱ ኳሶች በመልሶ ማጥቃት እድሎችን ለመፍጠር ሊሞክሩ ይችላሉ።በተለይ የፊት አጥቂዎቹ ቢስማርክ አፖንግ ና ቢስማርክ አፒያ የዚህ እንቅስቃሴ ቁልፍ ተጨዋቾች ሊሆኑ እንደሚችሉ ይገመታል።በተጨማሪ መሀል ሜዳ ላይ ሚሰለፋት አፈወርቅ ሀይሉ ና ይሁን እንደሻው ቡድናቸው ከመከላከል ወደ ማጥቃት በሚሸጋገርበት ወቅት ሚና ትልቁን ቦታ ሚይዝ ይሆናል።ከሜዳቸው ውጪ መጥፎ ክብረ ወሰን ያላቸው ሀድያዎች መጥፎ አጀማመራቸውን ለማስተካከል ከዚህ ጨዋታ ነጥብ ይዞ መውጣት ግድ ያላቸዋል።