የኢትዮጲያ ፕሪምየር ሊግ 12ኛ ሳምንት ነገ እሁድ የሚደረገው የወላይታ ድቻ እና ድሬዳዋ ከተማ ግጥሚያ ከጨዋታ በፊት ነጥቦችን አንስተንላቹሀል።
የጦና ንቦች ምንም እንኳን ባለቀ ደቂቃ በተቆጠረባቸው ግብ በሀዋሳ ሽንፈት አስተናግደው ቢመለሱም። የተከተሉት የአጨዋወት መንገድ አሁንም በነገው ጨዋታ የሚከተሉ ከሆነ ተጋባዦቹ ነጥብ ይዘው ለመውጣተ በጣም ከባድ ፈተና ይጠብቃቸዋል። በእርግጥ ግብ የማስቆጠር ችግር የማይስተዋልባቸው ቡርቱካናማዎቹ ከጨዋታ ጨዋታ እየተሻሻለ ያለውን የወላይታ ድች የተከላካይ ክፍል ሰብሮ ለመግባት ትልቅ ፈተና ይጠብቃቸዋል ተብሎ ሲጠበቅ። ግቦችን በቀላሉ የሚያስናግደው የተከላካይ ስፍራቸው ደግሞ በቀላሉ ዋጋ እንዳያስከፍላቸው የሚያሰጋቸው ጉዳይ ነው። ከጨዋታ ጨዋታ ግቦችን እያስቆጠረ የሚገኘው ሙህዲን ሙሳም የድቻን የመከላከል መስመር ሊረብሽ እንደሚችል የማያጠራጥር ጉዳይ ነው። በሁለቱም ቡድኖች በኩል በጉዳትም ሆነ በቅጣትም የሚያጣው ተጫዋች የሌለ ሲሆን። በወላይታ ድቻ በኩል የደጉ ደበበ ከጉዳቱ መመለስ ደግሞ መልካም ዜና ነው።
የእርስ በእርስ ግንኙነት
- ማሰታውቂያ -
ሁለቱም ቡድኖች በሊጉ መገናኘት የጀመሩት ከ2008 ጀምሮ ሲሆን። በጠቅላላ 6 ግዜ ተገናኝተው። ወላይታ ድቻ በአንድም አጋጣሚ ቡርቱካናማዎችን አሸንፈው አያውቁም። ሶስቱን ድሬዳዋ ሲያሸንፍ በቀሪው አቻ ተለያይተዋል። እሁድ 9:00 የሚደረገው የሁለቱም ቡድኖች ጨዋታ ሶዶ ላይ በፌደራል ዳኛ እያሱ ፈንቴ ይመራል።