ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች
ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ ቀናችን እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ
አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል
በሀገር ውስጥ ዘገባችን አዲስ አበባ ከተማን ለፕሪሚየር ሊጉ ያበቃው አሰልጣኝ እስማኤል አቡበከር እንግዳችን ነው…. አሰልጣኙ ከዮሴፍ ከፈለኝ ጋር በነበረው ቆይታ
እንደገለጸው “ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ አብዛኞቹ አሰልጣኞች ይልቅ 100 ፐርሰንት ጨዋ ነኝ ብዬ አምናለሁ” ሲል
“ከእግርኳሱ የምሰናበተው ወይ አይበላ ወይ አያስበላ ተብዬ ነው” የሚል ድፍረት የተሞላውን ምላሹን ሰጥቷል።
*….የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት ባለፈው ረቡዕ ለሊት ተጠናቋል.. በመጨረሻው ቀን ከተፈጸሙ ዝውውሮች አንዱ የጌታነህ ከበደ ዝውውር ነው በዝውውሩ ለጌታነህ ከበደ ፊርማ የቀረበለት ደመወዝና መሬት ግን አነጋጋሪ ሆኗል…
- ማሰታውቂያ -
*….ባለፈው ሳምንት ፊቱን ወደ በርሊን ያዞረው የአለም አትሌቲክስ አፍቃሪያን ፊት ነገ ደግሞ ወደ እንግሊዟ ለንደን ከተማ ይሆናል…በተጠባቂው የለንደን ማራቶን ደግሞ ኢትዮጵያዊያኑ ሹራ ኪታታና ብርሃኔ ለገሠ ይጠበቃሉ…በለንደን ማራቶኑ ዙሪያ ይስሃቅ በላይ ያዘጋጀው ዘገባ ተካቷል…
*.. ባህርዳር ከተማ በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ ቀርቧል…የጨዋታ ኮከብ የመሆን ዕድል ካገኙ ተጨዋቾች መሃል አንዱ የሆነው አህመድ ረሺድ ከመሸሻ ወልዴ ጋር በነበረው ቆይታ “በሲቲ ካፑ ያሳየነው ብቃት በፕሪሚየር ሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ ያደርገናል”ሲል ተናግሯል።ስለ ኮከብነቱም ሲናገር “ባለቤቴ በተመለከተችው ጨዋታ ኮከብ ተብዬ በመሸለሜ ደስ ብሎኛል” ሲልም አክሏል።
*….ስለ አዲስ አበባ ከተማ ዋንጫም የተዘጋጀ መረጃ ይዘናል…..
በውጪው ዘገባዎቻችን ደግሞ…
*…ከፍጻሜ በፊት ፍጻሜ የተሰኘው የሊቨርፑልና ማን.ሲቲ ጨዋታ ነገ አንፊልድ ላይ ይካሄዳል..የአሰልጣኞቹ የየርገን ክሎፕና ፔፕ ጋርዲዮላ የታክቲክ ጦርነት ይጠበቃል ስለ ጨዋታው መረጃዎችን ይዘናል….
*….አርሰናል ከተከታታይ ሽንፈት በኋላ አገግሟል… ለዚህ ደግሞ ወጣቱ ኢሚል ስሚዝ ሮው አስተዋጽዎው የጨመረ ነው
በአርሰናል ቤት እየደመቀ የመጣው ትንሹ ኮከብ የሰጠውን ቃለ ምልልስና ሌሎች መረጃዎችን አካተናል..
*…. ማን.ዩናይትድ ቪያሪያልን ባለቀ ሰአት በተቆጠረው የክርስቲያኖ ሮናልዶ ግብ ረቷል የቡድኑ ወሳኝ ተጨዋች ብሩኖ ፈርናንዴዝ ደግሞ ” ቪያሪያልን አሸንፈን የዩሮፓ ሊጉን ሽንፈት እንደምንበቀል እምነቱ ነበረን” ሲል ውጤቱ የጠበቁት መሆኑን ተናግሯል….
*….ኖርዊያዊው የማን.ዩናይትድ አለቃ ኦሊጉናር ሶልሻየር አስተማማኝ ቡድን መገንባት ተቸግሯል…. በዚህ የዩናይትድ እንቆቅልሽ ዙሪያ መረጃዎችን አካተናል…
*…የሊቨርፑሎቹ አሊሰን ቤከርና ፋቢንሆ
ይናገራሉ… “የውድድር ዘመኑ በምንፈልገው መልኩ እየሄደ ነው ለሲቲም ተዘጋጅተናል”በማለት ፋቢንሆ ሲፎክር አሊሰን ቤከር በበኩሉ “በአንፊልድ ያለው የደጋፊዎች ድባብ የተለየ ነው” ሲል ተናግሯል…
እናም ሌሎች መረጃዎች….
እርስዎ ብቻ ቀጠሯችንን አክብረው ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ ተዝናንተው ቁምነገር የሚጨብጡበት አዳዲስ መረጃዎችን የሚያገኙበት ይሆናል…..
ቅዳሜና እሁዳችሁ
የተባረከ ይሁን……