በ18ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብሮች ዛሬ በተለያዩ ከተሞች ተካሂደዋል።
በ9 ሰዓት በተደረጉ ጨዋታዎች፥ አዲስ አበባ ላይ ጅማ አባ ቡናን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጨዋታውን ያለ ምንም ጎል በአቻ ውጤት አጠናቋል።
በተመሳሳይ አርባ ምንጭ ላይ አርባ ምንጭ ከተማ ከሃዋሳ ከተማ ያለምንም ጎል አቻ በሆነ ውጤት ተለያይተዋል።
ድሬዳዋ ላይ የተካሄደው የድሬዳዋ ከተማና የሲዳማ ቡና ጨዋታም በተመሳሳይ ያለ ግብ አቻ ተጠናቋል።
ሲጠበቅ የነበረውና ጎንደር ላይ የተካሄደው የፋሲል ከተማና እና የኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ ደግሞ በኢትዮጵያ ቡና 4 ለ 1 አሸናፊነት ለኢትዮጵያ ቡና ጎሎቹን ኤሊያስ ማሞ ሳሙኤል ሳኑሚ አስቻለው ግርማና ጋቶች ፓኖም አስቆጥረዋል::
አዳማ ላይ ወላይታ ዲቻን ያስተናገደው አዳማ ከተማ ደግሞ 1 ለ 0 በማሸነፍ ወደ አሸናፊነት መመለስ ችሏል።ሙጂብ ቃሲም በመጀመሪያው አጋማሽ የአሸናፊነቷን ጎል አስቆጥሯል።