የ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን /
ዋልያዎቹ/ በካሜሮን አስተናጋጅነት
ለሚካሄደው የቻን አፍሪካ ዋንጫ
ለማለፍ የመጨረሻውን የማጣሪያ እና የመልስ
ጨዋታ የፊታችን እሁድ ከሩዋንዳ አቻው ጋር
ያደርጋል፤ ለእዚህም ጨዋታው ከቀናቶች
በኋላ ወደ ኪጋሊ የሚጓዝ ሲሆን የቅድመ
ዝግጅቱንም ከዛሬ አንስቶ የባህር ዳር ከተማ
ላይ መስራት ይጀምራል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለቻን አፍሪካ
ዋንጫ ለማለፍ የመጀመሪያ የማጣሪያ
ጨዋታውን ከጅቡቲ አቻው ጋር በደርሶ
መልስ አድርጎና በጣም ተፈትኖ ማሸነፍ
የቻለ ሲሆን ከ10 ቀናቶች በፊት ከሩዋንዳ
ጋር በመቐለ ኢንተርናሽናል ስታዲየም
ያከናወነውን የሜዳው ላይ ጨዋታ ደግሞ
የ1-0 የሽንፈት ውጤትን በማስመዝገብ
የአገራችንን ኳስ ወዳድ ህዝብ በጣም
ማስከፋቱና ማሳዘኑም ይታወሳል፡፡
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በቻን አፍሪካ
ዋንጫ ባደረጋቸው የእስካሁን ተሳትፎዎቹ
ለሁለት ጊዜያት ያህል የሩዋንዳንና የኬንያ
ብሄራዊ ቡድኖችን በአጠቃላይ የደርሶ መልስ
ጨዋታው ባስመዘገበው ውጤት በመጣል
በደቡብ አፍሪካና በሩዋንዳ የተዘጋጁት
ውድድሮች ላይ መሳተፉ የሚታወስ ሲሆን
በጊዜው ባደረጋቸው ጨዋታዎችም ዝቅተኛ
ውጤትን በማስመዝገብ የአገራችን እግር
ኳስ በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝም ጥቆማ
መስጠቱም ይታወቃል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለእዚሁ የቻን
አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ የፊታችን
እሁድ ከሩዋንዳ አቻው ጋር ስለሚያደርገው
ፍልሚያና ሌሎችን ጥያቄዎች አስመልክቶ
ከብሔራዊ ቡድናችን የተከላካይ ስፍራ
ተጨዋች ደስታ ደሙ ጋር ቆይታ ያደርግን
ሲሆን ተጨዋቹም ለቀረቡለት ጥያቄዎች
የሚከተሉትን መልሶች ሰጥቷል፡፡
ሀትሪክ፡- ለካሜሮኑ የቻን አፍሪካ ዋንጫ
ለማለፍ ሩዋንዳን በሜዳችሁ እና በህዝባችሁ
ፊት በመግጠም ሽንፈትን አስተናግዳችኋል፤
የተመዘገበው ውጤት ምን ስሜትን
ፈጠረባችሁ?
ደስታ፡- በሩዋንዳ የደረሰብን የሜዳችን
ላይ ሽንፈት እኛን የብሄራዊ ቡድን ተጨዋቾች
ብቻ ሳይሆን መላውን የአገራችንንም ኳስ
ወዳድ ህዝብ በጣም ያሳዘነ ፍልሚያ ነው፤
ልክ ጨዋታው እንደተጠናቀቀ ሁላችንም
ደስተኛ አልነበርንም፤ በጣም ነበር
የተናደድነው፤ በሽንፈቱ በከፍተኛ ሁኔታም
የቁጭት ስሜት ተሰምቶናል፡፡
ሀትሪክ፡- በሩዋንዳ የደረሰባችሁን የሜዳ
ችሁ ላይ ሽንፈት በኪጋሊው የመልስ ጨዋታ
የምትበቀሉ ይመስልሃል?
- ማሰታውቂያ -
ደስታ፡- አዎን፤ ለምን አንበቀልም፤
የመጀመሪያው ጨዋታ ላይ እኮ የእኛ
ቡድን በኳስ ቁጥጥርም ሆነ የጎል ዕድሎችን
በመፍጠር በኩል ከእነሱ የተሻለ ነበር፤ ያም
ሆኖ ግን ያገኘናቸውን የግብ አጋጣሚዎች
ባለመጠቀማችንና ሩዋንዳዎች ደግሞ በመልሶ
ማጥቃት አጨዋወት ያገኙትን አንድ የግብአጋጣሚ ስለተጠቀሙ ሊያሸንፉን ችለዋልና
ከዚያ በመነሳት ቡድናችን በክፍተቶቹ ላይ
ሰርቶ በመምጣትና ኳሱን ይዞ በመጫወት
ውጤቱን ከፈጣሪ እርዳታ ጋር የምንቀለብሰው
ይመስለኛል፡፡
ሀትሪክ፡- በሩዋንዳዎች የተሸነፍንበት
ምክንያት ምንድን ነው ትላለህ?
ደስታ፡- የሩዋንዳ ብሔራዊ ቡድንን በተፋ
ለምንበት የሜዳችን ላይ ጨዋታ ሽንፈትን
ልናስተናግድ የቻልንበት ዋንኛው ምክንያት
በሁላችንም ተጨዋቾች ውስጥ ግጥሚያውን
ለማሸነፍ የነበረን ጉጉት ከፍተኛ ስለነበር
ነው፤ ሩዋንዳዎች ወደ እኛ ሀገር የመጡት
ውጤቱን አጥብበው ለመሄድ ነበር፤ ያም
ሆኖ ግን የአንድ አንድ ሀገራት ብሔራዊ
ቡድን ከሜዳቸው ውጪ የሚያደርጓቸው
ጨዋታዎች ላይ ያገኙትን አንድ አጋጣሚ
በመጠቀምና ለመልሱም የሜዳቸው ጨዋታ
ላይ ውጤቱ እንደሚረዳቸው ስለሚያውቁ
ሩዋንዳዎችም ያንን ዕድል በመጠቀም ነው
ሊያሸንፉን የቻሉት፡፡
ሀትሪክ፡- ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን
በመመረጥ እየተጫወትክ ይገኛል፤ ለሀገር
የመጫወት ስሜቱ ምን ይመስላል?
ደስታ፡- ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን
ተመርጦ መጫወት መቻል ያለው ስሜት
በጣም ደስ ይላል፤ ሀገርህን የምታገለግልበት
የውድድር መድረክ ስለሆነም ያለው እርካታም
ከፍተኛ ነው፤ በእስካሁኑ የዋልያዎቹ ስብስብ
ቆይታዬ ለሶስት ጊዜያት ያህል ተመርጬ
ሀገሬን ለማገልገል ችያለሁ፤ ወደፊትም
በበርካታ ጨዋታዎች ላይ በመሰለፍ የብሄራዊ
ቡድናችንን መጥቀምና ውጤታማም ማድረግ
እፈልጋለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን
ተጨዋችነትህ ባሻገር አሁን ላይ ቅዱስ
ጊዮርጊስን ለማገልገል ፊርማህን አኑረሃል፤
እንዴት ወደ ቡድኑ ልታመራ ቻልክ?
ደስታ፡- ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገብቼ
እንድጫወት ሁኔታዎች የተመቻቸልኝ
በክለቡ በጥብቅ በመፈለጌ ነው፤ ለእዚህም
መጀመሪያ የቡድኑ ረዳት አሰልጣኝ ዘሪሁን
ሸንገታም ነበር የሊጉ ውድድር ሊጠናቀቅ
ጫፍ በደረሰበት ጊዜያት ለክለቡ እንድጫወት
ያናገረኝና ያኔ ከክለቡ ትልቅነት አንጻር አይኔን
ሳላሽም ነበር ፊርማዬን ማኖር የቻልኩት፡፡
ሀትሪክ፡- በእግር ኳስ ተጨዋችነትህ
አሁን ላይ ያለህበትን ደረጃ በምን መልኩ ነው
የምትገልጸው?
ደስታ፡- በእግር ኳሱ የአሁን ሰዓት ላይ
ያለሁበት ደረጃ ገና የጀማሪ ያህል ተጨዋች
ነኝ፤ ትልቅ ተጨዋች ነኝም ብዬ አላስብም፤
ወደፊት ግን የሀገሪቱ ትልቅና ውጤታማ
ተጨዋች ለመሆን ስለምፈልግ ብዙ ነገሮች
ላይ በርትቼ እሰራለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- በእግር ኳስ ተጨዋችነት ያሳለ
ፍከውን ህይወት በምን መልኩ ትገልጸዋለህ?
ደስታ፡- የኳስ ተጨዋችነት የእስካሁን
ህይወቴ በጣም ጥሩና ከፍተኛ መሻሻልንም
ያሳየሁበት ነው፤ ከሙገር ሲሚንቶ ክለብ
አንስቶ በደደቢትና በወልዋሎ አዲግራት
ዩንቨርስቲ ቡድኖች ቆይታዬ በስኬታማነት
መልኩ ኳሱን ለመጫወት ችያለሁ፤ የአሁን
ሰዓት ላይም በጥሩ ተጨዋችነቴ ለኢትዮጵያ
ብሔራዊ ቡድን ተመርጦ እስከመጫወት
ደረጃ ላይም ለመድረስ ችያለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ባታመራ
ኖሮ ወደ የትኛው ክለብ ልትዘዋወር ነበር?
ደስታ፡- ኢትዮጵያ ቡና፣ አዳማ ከተማ
ወይንም ባህር ዳር ከተማ የእኔ ማረፊያ
ቡድኖች ይሆኑ ነበር፤ ያም ሆኖ ግን ቅዱስ
ጊዮርጊስ አስቀድሞ ፈላጊዬ ክለብ ስለሆነ ወደ
እነሱ አምርቻለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የፕሪ
ሲዝን ልምምድን ጀምረሃል፤ እያደረጋችሁ
ያለውን ዝግጅት እንዴት ትመለከተዋለህ?
ደስታ፡- ቅዱስ ጊዮርጊስ በአዲሱ የባህር
ማዶ አሰልጣኝ እየሰራ ያለው የፕሪ ሲዝን
ዝግጅት በጣም ጠንካራና እየወደድኩትም
ያለ ሲሆን እስካሁንም አሰልጣኙ ሊከተል
ላሰበው የፕሬሲንግ አጨዋወቱ የሚሆንም
ልምምድን እያሰራን ይገኛል፤ እኛም የእሱን
ታክቲክ ለመተግበርም የአሁን ሰዓት ላይ
በሁሉም መልኩ ተዘጋጅተናል፡፡
ሀትሪክ፡- በመጨረሻ….?
ደስታ፡- የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብን የአሁን
ሰዓት ላይ ለመቀላቀል መቻሌ ከሚገባው
በላይ እያስደሰተኝ ይገኛል፤ በእዚህ ቡድን
በሚኖረኝ ቆይታም በርካታ ዋንጫዎችን
ከቡድኑ ጋር ማግኘት ስለምፈልግ እነዛን ለማ
ሳካት ጥረትን አደርጋለሁ፤ ይሄን ካልኩ በኋላ
በእስካሁኑ የኳስ ህይወቴ ከእኔ አጠገብ ሆነው
የረዱኝን አካላቶች ለማመስገን እፈልጋለሁ፤
መጀመሪያ ፈጣሪዬን ከዛ በመቀጠል ደግሞ
ቤተሰቦቼን፣ ያሰለጠኑኝን አሰልጣኞች ግርማ
ሀብተዩሃንስን፣ ኤልያስ ተሻለንና ፋሲል
ቡታን እና ጓደኞቼን አመሰግናቸዋለሁ፡፡