የካፍ የ2018/19 የቻምፒዮንስ ሊግ ድልድል ትላንትና ይፋ ሆንዋል በዚህም መሰረት የ2010 የኢትዮጰያ ፕሪሚየርሊግ አሸናፊ የሆነው ጅማ አባጅፋር የመጀመርያ ዙር የጥሎ ማለፍ ተጋጣሚውን አውቋል። በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ አሸናፊው የሆነው ጅማ አባጅፋር ከ ጅቡቲው አሸናፊ የሆነው ኤኤስ ጅቡቲ ቴሌኮሞ ጋር ተመድብዋል። ይህም ጨዋታ በካፍ ፕሮግራም መሰረት የመጀመርያው ዙር ህዳር 18 ወይም 19 ሲደረግ የመለሱ ጨዋታ በሳምንቱ ህዳር 25/26 አዲስ አበባ ላይ የሚጫወቱ ይሆናል።
የዚሁ ጨዋታ አሸናፊ በሁለተኛው ዙር የግብፁን አልሀሊ የሚገጥም ይሆናል ጅማ አባጅፋር የጅማ ዩኒቨርሲቲ ስቴድየም ባለመጠናቀቁ ጨዋታው አዲስ አበባ ስቴድየምን በማስመዝገቡ አዲስ አበባ ላይ የሚጫወት ይሆናል