በ27ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ቀጥሎ ውሏል።
ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም ሁለት ጨዋታዎች የተደረጉ ሲሆን፥ 8 ሰዓት ከ30 ላይ መከላከያ ከድሬዳዋ ከተማ ያስተናገደበት ጨዋታ አንዱ ነው።
ጨዋታውም በመከላከያ 1ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል።
- ማሰታውቂያ -
በጨዋታው ባዬ ገዛኸኝ በ39ኛው ደቂቃ ላይ ለመከላከያ ብቸኛዋን የማሸነፊያ ጎል ከመረብ አሳርፏል።
10 ሰዓት ከ30 ላይ ደግሞ በ24 ነጥብ ወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኘው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲዳማ ቡናን አስተናግዷል።
የሁለቱ ክለቦች ጨዋታም 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት መጠናቀቅ ችሏል።
በጨዋታው ላይ ሲዳማ ቡና ሙሉአለም መስፍን በ19ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠራት ጎል መምራት ችለው የነበረ ሲሆን፥ ጋብርኤል አህመድ በ86ኛ ደቂቃ ላይ ያስቆጠራት ጎል ንግድ ባንክ በሜዳው ነጥብ ተጋርቶ እንዲወጣ አስችሎታል።