ኤስፒራንስ ዲ ቱኒዝ ተቀናቃኙን ኤቷህል ዶ ሳህለን በማሸነፍ ጣፋጭ ሶስት ነጥብ አግኝቷል።
ትልቅ ግምት ተሰጥቶት የነበረው አጓጊው የቱኒዚያው ደርቢ ሀምዶ ኤል ሆኒ ሰላሳ ሁለተኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠራት ብቸኛው ግብ ኤስፒራንስ ዲቱኒዝ የበላይነት ተጠናቋል። የቤት ስራቸውን በሚገባ የተወጡት ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ በአምላክ ተሰማ ሁለት የቢጫ ካርዶችን ብቻ በ ኤትዋል ዴ ሳህል ተጫዋቾች ላይ መዘዋል። ኤስፒራንስ ዲ ቱኒዝ ነጥቡን ወደ 28 ከፍ ማድረግ የቻለበት ውጤት ማስመዝገብ ችሏል።