- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋልያዎቹ በካሜሩን አስተናጋጅነት
- ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የጋና ብሔራዊ ቡድንን
- ብላክስታሮችን በኩማሲው ባባያራ ስታዲየም ይፋለማል፤
- ዋልያዎቹ በማጣሪያው ጨዋታ በምድባቸው ከጋና፣ ከሴራሊዮንና
- ከኬኒያ ብሔራዊ ቡድኖች ጋር የተደለደሉ ሲሆን ለእዚህም ወሳኝ
- ጨዋታ ቡድኑ 22 ተጨዋቾችን በመያዝ ነው ወደ ስፍራው ሐሙስ
- ዕለት ያመራው፡፡
- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለእዚህ ወሳኝ ጨዋታም ልምምዱን
- ከሌላው ጊዜ አኳያ ሰፋ ያለ ጊዜ ወስዶ ሲሰራ የከረመ ሲሆን
- ለቡድኑም ከተመረጡት ተጨዋቾች መካከል በፕሮፌሽናል
- ተጨዋችነት በግብፅ ሊግ የሚጫወቱት ሽመልስ በቀለና ኡመድ
- ኡኩሪም ስኳዱን ተቀላቅለው ጠንካራ ልምምዳቸውን ከቡድኑ ጋር
- ሲሰሩም ከርመዋል፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የጋና ብሄራዊ
- ቡድንን በጥሩ ሁኔታ ለመፋለም እና የራሱንም አቋም ለማወቅም
- የአቋም መለኪያ ግጥሚያዎችንም ያደረገ ሲሆን
- የመጀመሪያውንም ኢንተርናሽናል የአቋም መለኪያ ጨዋታውን
- በሰርቢያዊው አሰልጣኝ ሚቾ ከሚመራው የኡጋንዳ ብሄራዊ ቡድን
- ጋርም ባለፈው ሳምንት በሐዋሳው ኢንተርናሽናል ስቴድየም ላይ
- በማድረግ 0-0 በሆነ ውጤትም ሊያጠናቅቅም ችሏል፡፡
- በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ የሚመሩት የዋልያዎቹ ስብስብ
- በእስካሁን የዝግጅት ጊዜያቸው ከመከላከያ ተስፋ ቡድንና ከፋሲል
- ከተማ ቡድን ጋርም ያንን ያህል የቡድኑን አቋም የሚለካ
- ባይሆንም የሟሟቂያ ግጥሚያም አድርገው 5-0 እና 3-0
- ያሸነፉበት ግጥሚያ የሚጠቀስ ነው፣ ዋልያዎቹ ዛሬ ጋናን
- ለሚፋለሙበት ጨዋታም ከግጥሚያው ጠንካራነት አንፃር እልህ
- አስጨራሽ ፍልሚያ ይጠብቀዋል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ቡድኑ
- ከሌሎች ጊዜ አጨዋወቶቹ አኳያ ለውጥ አድርጎ ከመጣ፣
- መከላከሉ ላይ ብቻ ትኩረት ካላደረገ እና ኳስን ተቆጣጥሮና እንደ
- ቡድን በመከላከል እና በማጥቃት ላይ አተኩሮ ከተጫወተ ጥሩ
- ውጤት ይገጥመዋል ተብሎ እየተጠበቀም ነው፤ የኢትዮጵያ
- ብሔራዊ ቡድን በዛሬው ዕለት ከጋና ጋር በሚያደርገው
- የመጀመሪያው ጨዋታ ለዋልያዎቹ መልካም ውጤት
- እንዲገጥመው እንመኛለን፡፡
- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የዛሬን ጨዋታ በተመለከተ
- በማጣሪያው ስለሚኖረን የማለፍ ዕድል የቡድኑ አሰልጣኝ አሸናፊ
- በቀለን እና ከቡድኑ ተጨዋቾች መካከል አስቻለው ታመነን እና
- አብዱልከሪም መሐመድን አናግረን ምላሻቸውን ሰጥተውናል፡፡
- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ
- ‘‘በአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታው ማሸነፍ ብቻ አይደለም
- ቢሳካልንና ዋንጫውን ብንበላስ ብለን ብናስብ መልካም ነገር
- ነው”
- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋናን ለሚፋለምበት የዛሬው የአፍሪካ
- ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ የቅድመ ዝግጅቱን ሲሰራ ከርሟል፤
- የወዳጅነት ጨዋታንም ከኡጋንዳ ጋር አድርጓል፤ ከእነዚህ
- ዝግጅታችሁ ያገኛችሁት ጥቅም ምን ይመስላል?
- ‘‘ለካሜሮኑ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ያደረግነው ዝግጅት ጥሩ
- የሚባል ነው፤ በቆይታችንም የቡድናችንን ተጨዋቾች አንድነት፣
- ህብረት እንደዚሁም ደግሞ በግጥሚያው ላይ ጥሩ ውጤት
- ለማምጣት የሚችሉበትን መነሳሳትና ከፍተኛ የመጫወት
- ፍላጎትንም ልንመለከትበት ችለናል፤ የኡጋንዳ ብሄራዊ ቡድንን
- በተፋለምንበት የአቋም መለኪያ ጨዋታ ላይ ደግሞ
- የግጥሚያውን እድል ማግኘታችን ጠቀሜታው ጥሩ ነው፤ ያም
- ሆኖ ግን አቋማችንን ሙሉ ለሙሉ ለማወቅ የቡድናችን
- ተጨዋቾች የተጫወቱት 45 ደቂቃ ብቻ መሆኑ 90 ደቂቃው ምን
- ይመስላል የሚለውን ለማየት እድለኞች አልሆንንም፤ ያም የራሱ
- የሆነ ተፅህኖ አለው፤ እንደዛም ሆኖ ግን የኡጋንዳ ብሔራዊ
- ቡድን በምስራቅ አፍሪካ ጠንካራ ከሆኑት አገራት መካከል አንዱ
- ስለሆነ ከእነሱ ጋር የመጫወት እድል በማግኘታችን በእራሱ
- ያለንበትን ሁኔታ በተወሰነ መልኩም ቢሆን እንድናይ አድርጎናል”፡፡
- የኡጋንዳ ብሔራዊ ቡድንን ሐዋሳ ላይ በአቋም መለኪያ
- ስትፋለሙ የነበራችሁ ክፍተትና ጠንካራው ጎን ምን ነበር?
- ‘‘በወዳጅነት ጨዋታው ኡጋንዳን ስንገጥም በእኛ በኩል የነበረብን
- ዋንኛ ችግር ግብ ማስቆጠሩ ላይ ነው፤ የአጨራረስ ችግራችን
- ጎድቶናል፤ ይህ ችግር ደግሞ የሀገሪቱ የረጅም ጊዜ ክፍተትም
- ሊሆን ችሏልና ይህን በፍጥነት ልናርመው ይገባል፡፡ በተቃራኒው
- እኛ የነበረን ጠንካራ ጎን ደግሞ እንደህብረት የምንከላከልና
- የምናጠቃ መሆኑ ነው፤ ይህንን ብቃት ይበልጥም አጠናክረን
- ልናስቀጥለውም ተዘጋጅተንበታል”፡፡
- የጋናን ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ለመለፋም ተዘጋጅታችኋል፤ ስለእነሱ
- ወቅታዊ አቋም የቱን ያህል አውቃችኋል…. ከግጥሚያውስ ምን
- ውጤትስ ለማምጣት ነው እያሰባችሁት ያላችሁት?
- ‘‘የጋናን ብሔራዊ ቡድን ወቅታዊ አቋም በተመለከተ እነሱ
- በአፍሪካ ብቻ ሳይሆን በዓለም እግር ኳስ ላይም እንዳላቸው
- ጥንካሬ እውቅናና ብቃት ከተመለከትነው ነገር በመነሳት ብዙ
- ነገሮችን አውቀናል፤ ያንንም ብቃታቸውንም በጋራ ማጥቃትና
- በጋራ በመከላከልም በመጫወት ልንመከታቸውም ተዘጋጅተናል፡፡
- የጋናን ብሄራዊ ቡድን ዛሬ ስንገጥምም እኛ ወደሜዳ የምንገባው
- ከግጥሚያው ጥሩ የሚባል ውጤትን ይዘን ለመውጣት ነው፤
- ያንንም የማሳካት ብቃትም አለን፣ በጨዋታው ውጤታማም
- እንሆናለን”፡፡
- ዋልያዎቹን ለአፍሪካ ዋንጫ ከማሳለፍ ባሻገር ከምድቡም
- እናልፋለን ብለህ ነበር፤ ይህንን እንዴት ተመለከትከው፤
- የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን ከጋና ጋር ስታነፃፅረውስ ዋልያዎቹን
- በምን ደረጃ ላይ ታስቀምጣችኋለህ?
- ‘‘የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ
- ጨዋታዎቹ ላይ ግጥሚያዎቹን ማሸነፍ ብቻ አይደለም፤
- ቢሳካልንና ዋንጫውን ብንበላስ፤ ስለዚህ አንድ ነገርን ለማሳካት
- እስከመጨረሻው ሰዓት ድረስ መመኘትና ማሰብ መልካም ነገር
- ነውና ውጤታማስ ለምን አይኮንም፤ አሁን ልጆቹ ያላቸው ፍላጎት
- ጥሩ ነው፤ ከጋና ብሄራዊ ቡድን ጋር ስላለው ንፅፅር በሁለታችንም
- መካከል ሰፊ ልዩነት አለን፤ ለንፅፅርም ያለንበት ስፍራም
- አይመጥነንም፡፡ አሁን ባለን ትውልድም ከፍተኛ ለውጥ
- እናመጣለን ማለትም ከባድ ነገር ነው፤ እታች መስራት
- ያስፈልጋል፣ ላለንበት የእግር ኳስ ደረጃ ትኩረት ሊሰጥ
- ያስፈልገዋል. ህዝብ ባለሙያና መንግስትም በጋራ በመሆን
- የተቀናጀ ነገርም መስራት ያስፈልጋችኋል፡፡
- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተከላካይ አስቻለው ታመነ
- ‘‘ከጋና ዛሬ ነጥብ ተጋርተን የምንመለስ ይመስለኛል”
- ለካሜሮኑ የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ዛሬ ኩማሲ ላይ የመጀመሪያ
- ጨዋታችሁን ታደርጋላችሁ፤ ስለዝግጅታችሁና ስለጨዋታው ምን
- የምትለው ነገር አለ?
- ‘‘የአፍሪካ ዋንጫ የማለፍ ህልማችንን ለማሳካት በዝግጅታችን
- ወቅት በቴክኒክ፣ በታክቲክ እና በአህምሮአችን ላይ ጥሩ ነገርን
- ሰርተናል፤ ከዚህ ዝግጅታችን ጎን ለጎንም የአቋም መለኪያ
- ጨዋታንም ለማድረግ ችለናል፡፡ በጨዋታው ላይም ቡድኑ የራሱን
- ጠንካራና ደካማ ጎንም ሊያይበትም ችሏልና በእዚህ መልኩ ነው
- የተዘጋጀነው፤ ዝግጅታችንም ለጋናው ጨዋታ ብቻ ሳይሆን
- ዋልያዎቹንም ወደ አፍሪካ ዋንጫውም ለማሳለፍ ስለሆነ ያንን
- እልማችንንም የምናሳካውም ነው የሚሆነው፤ ስለዚህም
- ቡድናችን ከዛሬው ጨዋታ ላይ እንደ እኔ እምነትም ከጋና ነጥብ
- ተጋርተን የምንመለስም ይመስለኛል”፡፡
- የጋናን ብሔራዊ ቡድን በተመለከተ የዛሬው ጨዋታ ላይ ስለእነሱ
- ምን አይነት ግምትን ሰጥታችሁ ነው ወደሜዳ የምትገቡት?
- ‘‘የጋና ብሄራዊ ቡድን የአፍሪካ አህጉር ላይ ብቻ ሳይሆን በአለም
- ዋንጫም ላይ በመሳተፍ የሚታወቅ ትልቅ ቡድን እንደሆነ
- ሁላችንም ነው የምናውቀው፤ እነሱንም ባላቸው ችሎታና ብቃትም
- እናከብራችኋለን፤ እንጂ አንፈራቸውም፡፡ ጋና ትልቅ ቡድን ነው፤
- ነገር ግን የእግር ኳስ ጨዋታ ሁሌም ራስህን በወቅታዊ እና በ90
- ደቂቃም አቋምህም የምትለካበትና የምትመለከትበትም ስለሆነ
- እኛም ያንን አስበን ነው የጋናን ጨዋታ የምናደርገው፡፡
- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተከላካይ አብዱልከሪም መሐመድ
- ‘‘ጥሩ ስብስብ ስላለን ጋናን አሸንፈን አልያም ነጥብ ተጋርተን
- ለመመለስ ነው የምንፈልገው”
- የዋልያዎቹ ስብስብ ጋናን ዛሬ በአፍሪካ ዋንጫው የማጣሪያ
- ጨዋታ ላይ ይፋለማሉ፤ ስለ ዝግጅታችሁ ስለተጋጣሚያችሁና
- ስለግጥሚያው ምን ትላለህ…፡-
- ‘‘የአፍሪካ ዋንጫው ማጣሪያ ዝግጅታችን ጥሩ የሚባል ነው፤
- በመከላከልና በማጥቃቱም ላይ በምን መልኩ ማለትም ኳስ
- ስናገኝና ስናጣ እንዴት መጫወት እንዳለብን ከልምምዳችን
- በመነሳት እና በወዳጅነት ጨዋታውም ላይ ራሳችንን ለማሳየት
- በመሞከር አቋማችንን በሚገባ ተመልክተናል፤ የጋናውን
- ብላክስታር ወቅታዊ አቋም በተመለከተ ደግሞ እኛ ስለእነሱ
- ከተመለከትነው ቪዲዬ በመነሳት ስለአጨዋወታቸው ያወቅነው
- ነገር አለ፡፡ በጋራ ኳስን በማጥቃትና በመከላከል የሚጫወቱ
- ናቸው፤ አግሬሲቭ ሆነውና ጠንከር ብለውም ነው የሚጫወቱት፤
- እንደብዙዎች የአፍሪካ አገራትም የመስመር ላይ ኳስንም
- ይጠቀማሉና እኛ ያንን አይተንም ነው እነሱን ለመግጠም
- የተዘጋጀነው፤ ከጋና ጋር በሚኖረን ጨዋታ እኛ ወደ ሜዳ
- የምንገባው ግጥሚያውን ለማሸነፍ ነው፤ ያ ካልተቻለ ነጥብ
- ተጋርተን ለመምጣት ጥረትን የምናደርግ ይሆናል”፡፡
- የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከጋና፣ ከኬኒያ እና ከሴራሊዮን ጋር
- ከመደልደሏ አኳያ ወደካሜሮኑ የአፍሪካ ዋንጫ ታልፋለች?
- ‘‘የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታው ላይ ምንም እንኳን በእኛ
- ምድብ ጠንካራዋ ጋና ከእኛ ጋር ብትደለደልም አሁን ከያዝነው
- ጥሩ የተጨዋቾች ስብስብ አኳያ እኛ ወደ ካሜሩን የአፍሪካ ዋንጫ
- ለማለፍ ሰፊ እድል ነው ያለን፤ በመጀመሪያ በውድድሩ ተሳትፎ
- ላይ ራሳችንን አንድ ነገር መስራት እንደምንችል ማሳመን አለብን፡፡
- ለዚያም አዕምሮአችንን ማሳመን አለብን፡፡ ያንን ካደረግን
- የምንፈልግበት ደረጃ ለይ የማንደርስበት ምንም አይነት ምክንያት
- አይኖረንም”፡፡