በ17ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬም በመቀጠል ሰባት ጨዋታዎችን አስተናግዷል።
በዛሬው እለት አብዛኛው ጨዋታዎች በተመሳሳይ ዘጠኝ ሰዓት በክልል እና በአዲስ አበባ ስታዲየም ነው የተደረጉ ሲሆን፥ አንድ ጨዋታ ብቻ በ11:30 ላይ ተካሂዷል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም ሁለት ጨዋታዎች የተካሄዱ ሲሆን፥ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከድሬ ደዋ ከተማ እንዲሁም ኢትዮጵያ ቡና ከመከላከያ ተጫውተዋል።
ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከድሬ ደዋ ከተማ ዘጠኝ ሰዓት ያደረጉት ጨዋታም በኢትዮ ኤሌክትሪክ 3ለ1 አሸናፊነት ተጠናቋል።
- ማሰታውቂያ -
በጨዋታው ላይ በረከት ተሰማ በ43ኛ፣ ፍፁም ገብረማርያም በ87ኛ እንዲሁም የድሬ ደዋ ከተማው በረከት ሳሙኤል በ46ኛው ደቂቃ በራሱ ላይ ያስቆጠረው ጎል ኢትዮ ኤሌክትሪክን አሸናፊ አድርገዋል።
ድሬ ደዋን በባዶ ከመውጣት የታደገችውን ጎል በረከት ይስሃቅ በ30ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፏል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም የተደረገው ሌላ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡናን ከመከላከያ ያገናኘ ሲሆን፥ ጨዋታውም በኢትዮጵያ ቡና የበላይነት ተጠናቋል።
ኢትዮጵያ ቡና መከላከያን 4ለ0 በሆነ ውጤት በመርታትም ሙሉ 3 ነጥብ ይዞ መውጣት ችሏል።
በጨዋታምው ጋቶች ፓኖም በ36ኛው እና በ41ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት 2 ጎሎችን ከመረብ ሲያሳርፍ፤ ሳሙኤል ሳኑሚ በ47ኛው ደቂቃ ሶስተኛዋን ጎል እንዲሁም አብዱልከሪም መሃመድ 4ኛዋን ጎል በ90ኛው ለኢትዮጵያ ቡና አስቆጥሯል።
በክልል ከተደረጉ ጨዋታዎች ደግሞ ሀዋሳ ላይ ንግድ ባንክን ያስተናገደው ሀዋሳ ከተማ ባንክን 4ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
መድህኔ ታደሰ በ14ኛው ደቂቃ፣ ጃኮ አራፋት በ20ኛው ደቂቃ፣ ፍሬው ሰለሞን በ33ኛው ደቂቃ እንዲሁም ጋዲሳ መብራቴ በ52ኛው ደቂቃ ባስቆጠሩት ጎል ሀዋሳ ከተማ አሸናፊ ሆኗል።
ወልዲያ ላይ የተካሄደው የወልዲያ ከተማ እና የአርባ ምንጭ ከተማ ጨዋታ ደግሞ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።
በጨዋታው ላይ አንዷለም ንጉሴ በ47ኛው ደቂቃ ለወልዲያ ከተማ ሲያስቆጥር፤ አመለ ሚልኪያስ በ54ኛው ደቂቃ ላይ ለአርባ ምንጭ ከተማ ያስቆጠራት ጎል ጨዋታው በአቻ እንዲጠናቀቅ አድርጓል።
በሌላ ጨዋታ ፋሲል ከነማን በሜዳው ያስተናገደው ወላይታ ድቻም ድል የቀናው ሲሆን፥ ጨዋታውም በወላይታ ድቻ 2ለ1 አሸናፊነት ተጠናቋል።
አናጋው ባደግ በ26ኛው ደቂቃ እንዲሁም ተመስገን ዱባ በ54ኛው ደቂቃ ያስቆጠሩት ጎል ወላይታ ድቻን አሸናፊ ሲያደርግ፤ ለፋሲል ከነማ ደግሞ ብቸኛዋን ጎል ኤዶም ሆሮሶውቪ በ51ኛው ቀዲቃ ከመረብ አሳርፏል።
ይርጋለም ላይ አዳማ ከተማን ያስተናገድው ሲዳማ ቡናም በሜዳው ድል የቀናው ሲሆን፥ ጨዋታውም በሲዳማ ቡና 1ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል።
በጨዋታው ላይ ወሰኑ ማዜ በ45ኛ ደቂቃ ያስቆጠራት ጎል ሲዳማ ቡና በሜዳው ሙሉ 3 ነጥብ እንዲያገኝ አስችሏል።
ጅማ ላይ አዲስ አበባ ከተማን ያስተናገደው ጂማ አባ ቡናም በሜዳው ሙሉ 3 ነጥብ ይዞ መውጣት ችሏል።
ጨዋታምው 1ለ0 በሆነ ውጤት የተጠናቀቀ ሲሆን፥ ኪዳኔ አሰፋ በ21ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ጎል ጅማ አባ ቡናን አሸናፊ አድርጋለች።
# | ክለብ | ተጫ | ልዩ | ነጥብ | |
---|---|---|---|---|---|
1 | ![]() |
17 | 20 | 35 | |
2 | ![]() |
17 | 5 | 31 | |
3 | ![]() |
17 | 8 | 28 | |
4 | ![]() |
17 | 7 | 28 | |
5 | ![]() |
17 | 3 | 27 | |
6 | ![]() |
17 | 4 | 26 | |
7 | ![]() |
17 | 0 | 23 | |
8 | ![]() |
17 | 0 | 21 | |
9 | ![]() |
17 | -4 | 21 | |
10 | ![]() |
17 | -5 | 21 | |
11 | ![]() |
17 | -1 | 20 | |
12 | ![]() |
17 | 0 | 19 | |
13 |
|
17 | -4 | 17 | |
14 | ![]() |
17 | -10 | 16 | |
15 | ![]() |
17 | -13 | 14 | |
16 | ![]() |
17 | -10 | 10 |