በይስሀቅ በላይ ከካናዳ ኦታዋ
“ለውድድሩ ሠዓታት ሲቀሩት በውስጤ የተዘበራረቀ ስሜት ተፈጥሮ ነበር፤በተለይ ሌሊት ላይ የገጠመኝ ያልታሰበ የሆድ ህመም ውድድሬን በብቃት እንዳላሸንፍ ያደርገኝ ይሆን እንዴ?ብዬ እንድሰጋ አድርጎኝ ነበር በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለሁ አምላኬን አንተ ታውቃለህ ብዬ ውድድር ውስጥ ገብቼ ከገጠመኝ የሆድ ህመም ተጋላገልኩ ባልኩበት ሰዓት ሌላ ያልተጠበቀ የእግር ህመም ስሜት ተሰማኝ፤ቀደም ሲል የነበረብኝ የእግር ህመም ሲቀሰቀስብኝ ወዲያውኑ በቃ ዛሬ ቀኔ አይደለም የሚል ስሜት በውስጤ ተፈጠረ ነገር ግን የፈለገ ይሁን እግዚአብሔርም ከእኔ ጋር ሰለሆነ ህመሜን ረስቼ መሮጥና ማሸነፍ አለብኝ አልኩኝ አምላክም ረድቶኝ አሸነፍኩ”
- ማሰታውቂያ -
ይህንን ከላይ ያለውን ቃል የኦታዋ ማራቶን የ10k አሸናፊነቱን ለመጀመሪያ ጊዜ ካወጀ ከደቂቃዎች በኃላ በተለይ ለሀትሪክ ድረ-ገፅ ኦታዋ ላይ ለሀትሪክ ማኔጂንግ ኤዲተር ይስሀቅ በላይ የሰጠው ልዑል ገ/እግዚአብሔር ነው።
ትናንት በተካሄደው የኦታዋ ማራቶን የ10k የወንዶች ሩጫ ኢትዮጵያዊው የ24 ዓመት ወጣት ልዑል ገ/እግዚአብሔር ተፎካካሪዎቹን አሜሪካዊውና ኬንያዊያን አትሌቶችን ከኃላ አስከትሎ በመግባት አሸነፈ።
ልዑል ፍፁም ልዪ በሆነ የአጨራረስ ብቃትና ከፍተኛ ፍጥነት በኦታዋ ምድር የራሱንና የኢትዮጵያዊያንን አሸናፊነት 28:43 በሆነ ሰዓት ያወጀ ሲሆን አሜሪካዊው ማርቲን በ29:05 እንዲሁም ለአሸናፊነት ከፋተኛ ግምት የተሰጠው ኬንያዊው ኒኮላስ 29:33 በሆነ ሰዓት ሶስተኛ ሲወጣ ሌላው ኢትዮጵያዊ ቦንሳ ጎንፋ 30:07 በሆነ ሰዓት 7ኛ በመውጣት ውድድራቸውን አጠናቀዋል።
“10ኛ ክፍል እያለሁ ጀምሮ የቀነኒሳን ገድልና ውጤት እያየሁና እየሰማሁ እሱንም እያደነኩ ማደጌ ለዛሬ ማንነቴ አብቅቶኛል”የሚለው የ24 ዓመቱ ልዑል “ሁሌም በልምምዴና በሩጫዬ ወቅት እንደ ቀነኒሳ መሆን አለብኝ ብዬ ሞዴል አድርጌ መነሳቴ ውጤታማ እንድሆን ትልቅ መነሳሳትን ፈጥሮልኛል በጭሩ ቀነኒሳ በቀለ በእኔ የሩጫ ህይወት ውስጥ ትልቅ ቦታ አለው”የሚለው የኦታዋ ማራቶን የ10k አሸናፊ ልዑል “መጀመሪያ ከገጠመኝ መጠነኛ ህመም ውጭ ውድድሩን በአሸናፊነት እንደማጠናቅቅ እርግጠኛ ነበርኩም”ብላል ከውድድሩ በኃላ ይሄ ውጤት ምን መልዕክት ያስተላልፋል ተብሎ ከሀትሪክ ድረ-ገፅ ጥያቄ የቀረበለት ልዑል “ኦታዋ ላይ ያስመዘገብኩት ውጤት ትልቅ መልዕክት ነው የሚያስተላልፈው በቀጣይም ወደ ለንደኑ የአለም ዋንጫ ለሚደረገው ምርጫም ትኩረት እንዲረግብኝም ለመመረጥም ጠንክሬ እንድሰራ ያደርገኛል”ያለው ልዑል ድል ያደረገባትን ኦታዋን በተመለከተ ሲናገር”ኦታዋ ምርጥ ከተማ ናት ለማሸነፍ የሚመች የአየር ንብረትና ጥሩ የሚያበረታቱ ምርጥ ደጋፊዎች ያሉባት ከተማ ናት” ካለ በኋላ “በቀጣይ በሚደረገው ውድድርም መካፈል እፈልጋለሁም”ብላል።
ቀጣይ ዕቅዱን በተመለከተ በመጨረሻ ከሀትሪክ ድረ-ገፅ ጥያቄ የቀረበለት ልዑል “በቀጣይ ኦስትራቫ ላይ ለሚኒማ እሮጣለሁ በዚህ ውድድር ላይ ደግሞ ብዙ ጊዜ ኢትዮጵያውያንን በማሸነፍ የሚያበሳጨኝ ሞ ፋራህ ይሳተፋል በዚህ ውድድር ላይ ሚኒማ ከማማላት በተጨማሪ ሞ ፋራህን በማሸነፍ መበቀል እፈልጋለሁ።”በማለት አስተያየቱን አጠናቃል።
ልዑል ገ/ስላሴ የኦታዋ ማራቶን የ10k አሸናፊ በመሆኑ የ10 ሺ የካናዳ ዶላር ተሸላሚ ሆናል።
Picture source-http://wpmedia.ottawacitizen.com