በ18ኛ ሳምንት በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ደደቢት ድል ቀንቶታል።በሊጉ ያለፉት አምስት ጨዋታዎችን ማሸነፍ ያልቻለው ደደቢት በአዲስ አበባ ስታዲየም ወልድያ ከተማን አስተናግዶ 1 ለ 0 አሸንፏል።
ብቸኛዋን የማሸነፊያ ግብም ኮከብ ጎል አስቆጣሪው ጌታነህ ከበደ አስቆጥሯል።
ደደቢት በሊጉ ከተደረጉ 18 ጨዋታዎች መካከል ስምንት አሸንፎ በሰባቱ አቻ የወጣ ሲሆን በ3 ጨዋታዎች ተሸንፏል።
ወልድያ ከተማ በበኩሉ በሊጉ ከኤሌክትሪክ ቀጥሎ በርካታ ጨዋታዎችን (9) አቻ የወጣ ክለብ ነው።
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመከላከያ 11 ሰዓት 30 ላይ ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ ጊዮርጊስ ለአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ውድድር ወደ ኮንጎ ስላመራ አርብ መጋቢት 10 ቀን ተላልፏል።
ሊጉ እሁድ ቀጥሎ ስድስት ጨዋታዎችን የሚያስተናግድ ሲሆን፥ በአዲስ አበባ ስታዲየም ከቀኑ 9 ስዓት ከ30 ላይ ንግድ ባንክ ከጅማ ይገናኛሉ።
በተመሳሳይ ሰዓት ክልል ላይ አዳማ ከወላይታ ዲቻ፣ አርባምንጭ ከሀዋሳ ከተማ እንዲሁም ድሬዳዋ ከሲዳማ ቡና ይጫወታሉ።
አዲስ አበባ ከተማ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ 11 ስዓት ከ30 በአዲስ አበባ ስታዲየም ይገናኛሉ።
በሊጉ የሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ ጎንደር ፋሲለደስ ስታዲየም ላይ ፋሲል ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና የሚጫወቱ ይሆናል።
በሁለቱ ቡድኖች የመጀመርያ ዙር ጨዋታ ፋሲል ከተማ አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ ኢትዮጵያ ቡናን 1 ለ 0 ማሸነፍ ይታወሳል።
ፋሲል በሊጉ የመጀመርያ ዙር አስደናቂ ጉዞ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን፥ ኢትዮጵያ ቡና ሰርቪያውን አሰልጣኝ ኒቮሳ ቩሲሲቪችን ካሰናበተ ወዲህ በገዛኸኝ ከተማ እየተመራ ጥሩ ግስጋሴ ላይ ይገኛል፤ በደረጃ ሰንጠረዡም ከመሪዎች ተርታ መሰለፍ ችሏል።
የእሁዱ ጨዋታ ለሁለቱም ቡድኖች በደረጃ ሰንጠረዡ አንዳቸው ከሌላኛው ላለመራቅ የሚያደርጉት ወሳኝ ጨዋታ ይሆናል።
ሊጉን ቅዱስ ጊዮርጊስ በ35 ነጥብ ሲመራ ደደቢት እና ሲዳማ ቡና በ31፣ ኢትዮጵያ ቡና በ28 ነጥብ ተከታዩቹን ደረጃ ይዘዋል።
ጌታነህ ከበደ ደግሞ በ13 ግቦች ኮከብ ግብ አግቢነቱን ይመራል።
# | ክለብ | ተጫ | ልዩ | ነጥብ | |
---|---|---|---|---|---|
1 | ![]() |
17 | 20 | 35 | |
2 | ![]() |
18 | 9 | 31 | |
3 | ![]() |
18 | 5 | 31 | |
4 | ![]() |
17 | 7 | 28 | |
5 | ![]() |
17 | 3 | 27 | |
6 | ![]() |
17 | 4 | 26 | |
7 | ![]() |
17 | 0 | 23 | |
8 | ![]() |
18 | -1 | 21 | |
9 | ![]() |
17 | -4 | 21 | |
10 | ![]() |
17 | -5 | 21 | |
11 | ![]() |
17 | -1 | 20 | |
12 | ![]() |
17 | 0 | 19 | |
13 |
|
17 | -4 | 17 | |
14 | ![]() |
17 | -10 | 16 | |
15 | ![]() |
17 | -13 | 14 | |
16 | ![]() |
17 | -10 | 10 |
- ማሰታውቂያ -