ተወዳጇና ዘወትር ማክሰኞ ለንባብ የምትበቃው ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገም ከእናንተ እጅ ለመድረስ ዝግጅቷን አጠናቃ ወደ ማተሚያ ቤት ልታመራ ችላለች፤ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በነገው እትሟ ከሀገር ውስጥ ይዛሎት የምትቀርበው መረጃ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ የውድድር ተሳትፎ ሀገራችንን በመወከል የግብፁንና የአፍሪካውን ግዙፍ ክለብ ዛማሌክን በማሸነፍ ከውድድር ስላስወጣውና በውድድሩ ታሪክ አዲስ ወርቃማ ታሪክም ስላስፃፉት ወላይታ ድቻዎች /የጦና ንቦች/ የቀረበላችሁ ዘገባ የሚገኝ ሲሆን ከእዚያ ውጪ በፕሪምየር ሊጉ የአንደኛው ዙር የውድድር ተሳትፎው ለፋሲል ከተማ የተጫወተውና አሁን ደግሞ ከክለቡ ጋር ተለያይቶ መከላከያን የተቀላቀለው ዳዊት እስጢፋኖስ በእግር ኳስ ሕይወቱ ቀጣይ ቆይታው ዙሪያ ‘‘5 ዓመት የመጫወት ህልም አለኝ፤ ከምወደው ፋሲልና የጎንደር ህዝብ የተለየሁት ዓለሜ የምላቸው ሚስቴና ልጄ በልጠውብኝ” ነው ሲል በእዚህና በሌሎች ተያያዥ የሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ አስተያየቱን ሊሰጥ ችሏል፡፡ ሀትሪክ ስፖርት ሌላም መረጃን ይዛሎት ቀርባለች፤ ከእዚያ ውጪ በየሳምንቱ የቀድሞ እግር ኳሽ ተጨዋቾችን በምናስታውስበት የኦልዲስ በት ጉዲስ አምዳችን ላይ የእዚህ ሳምንት እንግዳ አድርገን ያቀረብንላችሁ በተጨዋችነት ዘመኑ ለ16 ዓመታት ከባህር ኃይል ወጣት ቡድን አንስቶ፣ ለህማኮ፣ ለሙገር፣ ለኢትዮጵያ ቡና፣ ለቅ/ጊዮርጊስ፣ ለኢትዮጵያ መድን፣ ለሐዋሳ ከነማና ለሐረር ቢራ የተጫወተው የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋችና የኳስ ሜዳው ተወላጅ ዮሴፍ ተስፋዬ /ቫንባስተን/ ሲሆን ከእሱ ጋር ሰፋ ያለ ቆይታን አድርገናል፤ ሀትሪክ ስፖርት ነገ እንዳታመልጦት፤ ሀትሪክ ስፖርት በባህር ማዶ ዘገባዎቿም በነገው እትም ይዛሎት የምትቀርበው ስለ አርሰናሉ ሁለገቡ የመድፈኞቹ ተጨዋች ኤነሪክ ሚኪታሪያን ተፅህኖ ፈጣሪነት የምናስነብባችሁ ሲሆን ከእዚያ ውጪም የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት ከተካሄዱት ጨዋታዎች መካከል ቡድናቸው ዋትፎርድን 5-0 ባሸነፈበት ጨዋታ ግብፃዊው ሞ. ሳላህ አራት ግቦችን ማስቆጠሩን ተከትሎ
“የሳላህ ደረጃ (ከሊዮኔል) ሜሲ እኩል ሆኗል” ብለው ስለሰጡት አስተያየት የቀረበላችሁ ዘገባ ይገኛል፤ ሌላው የሀትሪክ ስፖርት ዘገባ የባርሴሎናው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ በሻምፒዮንስ ሊግ ጉዞው ከክርስቲያኖ ሮናልዶ ጋር ሲነፃፀር በሚል የቀረበሎት መረጃም ይገኛል፡፡
ከእዚያ ውጪም ሌሎችም ሰፋፊ መረጃዎችን ከጋዜጣው ያነቡታል፡፡
በሌሎች የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች፤ የስፔን ላሊጋና የሌሎች ሊጎችንም አስመልክተን ከመዝናኛ አምዶቻችን ጋር ለእናንተ ሰፋ ያሉ መረጃዎችን አቅርበናል፡፡
በአውሮፓ የተለያዩ ሀገራት ስለተካሄዱ የውስጥ ውድድሮችም መረጃዎችን ይዛሎት ቀርባለች፤ ሀትሪክ የእናንተ ናት ይወዷታል፤ ያንብቧት
ሀትሪክ ሌሎች ያልተሰሙ አዳዲስና ትኩስ ዘገባዎችን ይዛሎት ቀርባለች፡፡
በርካታ አንባቢዎቻችን ባቀረባችሁልን ተደጋጋሚ ጥያቄ መሰረት ሀትሪክን በሳምንት ሁለት ቀን በቅርቡ ይዘን እንቀርባለንና ጠብቁን፡፡ ተጨማሪና ትኩስ መረጃዎችን በርካታ ተከታታዮች ባሉት hatricksport.com ድረ-ገፃችን ይጎብኙን፡፡
ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡
መልካም ንባብ
ተወዳጇና ዘወትር ማክሰኞ ለንባብ የምትበቃው ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገም ከእናንተ እጅ ለመድረስ ዝግጅቷን አጠናቃ ወደ ማተሚያ ቤት ልታመራ ችላለች፤ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በነገው እትሟ ከሀገር ውስጥ ይዛሎት ቀርባለች
Managing Editor at Hatricksport Website