ሶስቱ የሜዳሊያ ባለቤቶች በተለይ ለሀትሪክ ከለንደን
በይስሀቅ በላይ (ከለንደን)
በእግር ኳስ ያያና ኮሎ ቱሬ፣ ፍራንክና
ሮናልድ ዲቦር፣ ኤደንና ትሮጋን ሃዛርድ ወይም
ፊልና ጋሪ ኔቭልስ (የኔቭልስ ወንድማማቾች)
በቴኒስ የዊሊያምስ እህት ማማቾች እያልን
እንጠራለን፡፡ በአትሌቲክሱ ግን ለየት ያለ ነገር
ነው፡፡ የዲባባ ቤተሰቦች የአለማችን የፈጣን እግር
ባለቤቶች መሆናቸውን በርቀት አስመስክረዋል፡
፡ ለአፍሪካ በኦሎምፒክ የመጀመሪያዋን የወርቅ
ሜዳሊያ ያበረከተችውን ለሴት ኢትዮጵያዊያን
ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ሴት እህቶቻችን ፈር
ቀዳጅ በመሆን በር የከፈተችው አክስታቸው
አትሌቲ ደራርቱ ቱሉን የውጤታማነትና
የታሪክ ሰሪነት ዱካ ተከትለው የአትሌቲክሱን
አለም በይፋ የተቀላቀሉት የዲባባ ቤተሰቦች
ደራርቱ ቱሉ በቅብብሎስ የኢትዮጵያ ህዝብ
ኩራት መሆናቸውን ቀጥለዋል፡፡
የ3 ጊዜ የኦሎምፒክ የወርቅና ሜዳሊያና
የብር ሜዳሊያ ባለቤት የሆነችው የ32 አመቷ
ጥሩነሽ ዲባባ እጅግ ፈጣንና እልህ አስጨራሽ
በነበረው 16ኛው የለንደን አለም አትሌቲክስ
ሻምፒዮና የ10 ሺህ ሜትር የፈጣን እግር
ባለቤትና በርቀቱ የኦሎምፒክ ሪከርድን
በእጅዋ የያዘችውን አትሌት አልማዝ አያናን
ተከትላ በሁለተኛነት በማጠናቀቅ በአለም
አቀፍ ውድድር ሁለተኛውን የብር ሜዳሊያን
አስመዝግባለች፡፡ ባለፈው ቅዳሜ ከፍተኛ ቁጥር
ያለው ተመልካች በለንደን ኦሎምፒክ ስቴድየም
ተገኝቶ በተከታተለውና ከ202 በበለጠ አገራት
የቴሌቭዥን ስርጭት ባገኘው የለንደኑ የአለም
አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በሜዳሊያ
ሰንጠረዥ ውስጥ ያስገባ ወርቅና የብር ሜዳሊያ
በአልማዝ አያናና በጥሩነሽ ዲባባ ተመዝግቧል፡፡
3 ጊዜ የኦሎምፒክ አሸናፊ አምስት ጊዜ
የአለም አትሌቲክስ አሸናፊ ሁለት ጊዜ የአለም
ሻምፒዮና የብር ሜዳሊያ ባለቤት እንደሁም 3
ጊዜ የኦሎምፒክ ጨዋታዎች የነሐስ ሜዳሊያ
ባለቤት በመሆን በ10 ሺህ ሜትር የሩጫ
ውድድር ላይ በንግስና የቆየችው ጥሩነሽ
በጉዳትና ፊልዷን ወደ ማራቶን በመቀየርዋ
ላለፉት 11 ወራት አካባቢ ከውድድር ርቃ
ቆይታ የ3ቱን ኬኒያውያን የቡድን ስራ
አፈራርሳ ለራስዋና ለአገርዋ የብር ሜዳሊያን
ማስመዝገብዋ ብዙዎች ለውጤታማዋ አትሌት
አድናቆትን እንዲቸርዋት አስገድዷቸዋል፡፡
ባለፈው ቅዳሜ ለንደን በሚገኘውና ከ60
ሺህ ተመልካች በላይ በሚያስተናግደው የክዊን
ኤልዛቤት ኦሎምፒክ ስቴድየም አትሌት ጥሩነሽ
ዲባባ ውድድሯን ሁለተኛ ሆና በአሸናፊነት
ካጠናቀቀች በኋላ ሀትሪክ ጋዜጣን ጨምሮ
ከሌላው አለም ተውጣጥተው ለንደን ለከተሙ
የሚዲያ ሰዎች በሰጠችው ጋዜጣዊ መግለጫ
ባስመዘገበችው ውጤት እጅግ መደሰትዋን
ገልፃለች፡፡ የውድድር የፈጣን እግር ባለቤት
የሆነችው አልማዝ አያና ፈጣን አጨራረስ
መደመሟን በመናገርም አስተያየቷን የሰጠችው
አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ “አልማዝ አያና በጣም
ፈጣን አትሌት ናት፡፡ አሁን ባላት ፍጥነት እሷን
ማሸነፍ ከባድ ነው፤ ከእሷ ጋር ለመፎካከር
በደንብ ትሬኒንግ መስራት፤ ትራክ ላይ በቂ
ዝግጅት ማድረግ አለብኝ” በማለት የአልማዝን
ጥንካሬ አወድሳለች፡፡
በውድደሩ የሶስቱን ኬኒያዊያን የቡድን
ስራ አፈራርሳ ለራስዋና ለአገርዋ ከኬኒያዊያን
አፍ ላይ ነጥቃ ያመጣችው አትሌት ጥሩነሽ
ውድድሩን በሁለተኛነት በማጠናቀቅዋ
የተሰማትን ስሜት ስትገልፅ “አልማዝ ብቻዋን
በመውጣትዋ ቀሪው ፉክክር የነበረው በእኔና
በ3ቱ ኬኒያዊያን አትሌቶች መካከል ነበር፡፡
እነሱ በቡድን ስራ እኔን ለማድከም የተለያዩ
ዘዴ ቢቀይሱም እነሱን ቀድሜ ለመሄድ
እስከመጨረሻው እሞክር ነበር፡፡ በመጨረሻም
3ቱም ከእኔ ጋር እያሉ አሁን መሄድ አለብኝ
ብዬ ወጥቻለሁ፡፡ በመጨረሻም ያሰብኩትን
አሳክቻለሁ” በማለት የለንደኑ የአለም
አትሌቲክስ ሻምፒዮና የብር ሜዳሊያ ባለቤት
የሆነችው አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ተናገራለች፡፡
ቀደም ሲል ፊትሽን ወደ ማራቶን በማዞር
ማራቶን ስትሮጪ ነበር እንዴት ወደ 10 ሺህ
ሜትር ሩጫ በድንገት ሃሳብሽን ቀየርሽ በሚል
ጥያቄ የቀረበላት አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ “በ10ሺህ
ሜትር ብዙ ውድድሮችን አሸንፌያለሁ፡
፡ ዘንድሮ ግን በአብዛኛው የተወዳደርኩትና
የተዘጋጀሁት ለማራቶን ነበር፤ ነገር ግን 10
ሺህ ስለማውቀው መግባት አለብኝ ብዬ ገብቼ
የተሻለ ውጤት ለማምጣት ሞክሬያለሁ”
በማለት አስተያየቷን መስጠት የቀጠለችው
አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ የብር ሜዳሊያ ያገኘሽበት
የዘንድሮው የለንደኑ የአለም አትሌቲክስ
ሻምፒዮና የመጨረሻው የ10ሺህ ሜትር
ውድድርሽ ነው ወይ በሚል ለቀረበላት ጥያቄ
“እውነት ለመናገር በህይወቴ የሚያስደስተኝ
የትራክ ላይ ሩጫ ነው፤ ትራክ ላይ ብዙ ጊዜ
ሮጬያለሁ፤ አሸንፌያለሁ፤ አሁን ወደ ማራቶን
ገብቻለሁ፡፡ በቀጣዩ ማራቶን ልሩጥ ወይም 10
ሺህ አልወሰንኩም፡፡ ምን ልሮጥ እንደምችል
የሚያውቀው እግዚአብሄር ብቻ ነው” በማለት
በቀጣይ በትራክ ወይም በማራቶን ላይ ትገኛለሽ
ወይ ለሚለው ጥያቄ ቁርጥ ያለ ምላሽ ሳትሰጥ
በደፈናው አልፋዋለች፡፡
ከሴቶች 10ሺህ ሜትር የፍፃሜ ውድድር
በፊት የሴቶች የ1500 ሜትር ሩጫ የግማሽ
ፍፃሜ የማጣሪያ ውድድር ላይ ተካፋይ
የነበረችው ታናሽ እህትዋ ገንዘቤ ዲባባ
ለጥቂት በሰአት ብቻ ያለፈችበትን ውድድር
እያሟሟቅሽ ባለበት ሰአት ተከታትለሻል ወይ
ከተከታተልሽ ምን ተሰማሽ በሚል በመጨረሻ
ጥያቄ የቀረበላት የትራክ ሩጫ ንግስቷ አትሌት
ጥሩነሽ ዲባባ “ገንዘቤ የማጣሪያውን ውድድር
ስታደርግ እያሟሟቅን እከታተላት ነበር፤
መጀመሪያ ወደ ውድድር ስትገባ ማጣሪያውን
አንደኛ ወይም ሁለተኛ ሆና ታጠናቅቃለች
ብዬ ነበር ያሰብኩት፡፡ ነገር ግን በውድድሩ
የዚህን ተቃራኒ ሳይ በጣም ነበር የደነገጥኩት፡
፡ ከመውደቅ ተርፋ በሰአት ታልፋለች የሚል
ግምት ስላልነበረኝ በማጣሪያው ያየሁት ነገር
አስደንግጦኛል፤ ዋናው ነገር ለፍፃሜው ማለፍ
በመሆኑ ጥሩ ነው፤ አሁን አልፋለች በፍፃሜው
የሚሆነው ግን አይታወቅም” በማለት አትሌት
ጥሩነሽ አስተያየቷን አጠናቃለች፡፡
———————————-
ከወርቅም በላይ አልማዝ የሆነችው አልማዝ አያና የመጀመሪያውን ወርቅ ለሀገርዋ አበረከተች
- ማሰታውቂያ -
ድል ለኢትዮጵያ፤ ወርቅ ለኢትዮጵያ፤
ፍፁም የማይታመን፤ የሆነውን ሁሉ አምኖ
ለመቀበል የሚክበድ፤ በምድር ላይ ያሉት
ቃላቶች ሁሉ በትክክል ለመግለፅ የሚቸገሩበት
አንፀባራቂ ድል፤ ትናንት ምሽት ከወርቅም
በላይ በሆነችው አልማዝ ተመዘገበ። አትሌት
ጥሩነሽ ዲባባም ከወርቅ የማይተናነስ የብር
ሜዳሊያ በማስመዝገብ ኢትዮጵያውያኖች
በለንደን ሰማይ ስር ደምቀው እንዲያበሩ
አደረገች። የ25 ዓመቷ የዓለም የኦሎምፒክ
ሪከርድ ባለቤት የሆነችው አልማዝ አያና
ዓለምን ሁሉ ባስደመመ ፍፁም የሆነ
የአጨራረስ ብቃት የመጀመሪያውን የወርቅ
ሜዳሊያ ለሀገርዋ አስገኝታለች።
በለንደን በኩዊን ኤልዛቤት ኦሎምፒክ
ስታዲየም በተካሄደው የ16ኛው የዓለም
አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሁለተኛ ቀን የ10ሺ
ሜትር ውድድር አልማዝ አያና ከፍተኛ
ከወርቅም በላይ አልማዝ የሆነችው አልማዝ
አያና የመጀመሪያውን ወርቅ ለሀገርዋ አበረከተች
ፍጥነትን በያዘ የአጨራረስ ብቃት በማሸነፍዋ
ውድድሩን በአካል በስታዲየም ተገኝተውና
በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች በተከታተሉት
ሁሉ ከፍተኛ አድናቆትን አግኝታለች። በተለይ
በኦሎምፒክ ስታዲየም በእያንዳንዱ ዙር
ከተመልካቹ ሲሰጣት የነበረው ድጋፍ ፍፁም
ልዩ ነበር። በተሻለ ፍጥነት እንድታሸንፍም
ረድቷታል። አልማዝ አያና የመጨረሻዎቹን 3
ኪሎ ሜትሮች በ8.33 በሆነ የሠዓት ፍጥነት
መሮጧ ከብዙዎች አድናቆት እንዲጎርፍላት
አድርጓል።
አስገራሚ በሆነ አጨራረስ ሌሎች
ተፎካካሪዎቿን በመደረብ ከ300 ሜትር በላይ
በሆነ ርቀት የ10ሺ ሜትሩን ሩጫ 30:16:32
በሆነ ሠዓት ያሸነፈችው የኦሎምፒክ ሪከርድ
ባለቤትዋ አልማዝ አያና ድሉ ከእዛሬዎቹ
ድሎችዋ ሁሉ የተለየ ደስታን እንደፈጠረባት
ተናግራለች።
ላለፉት 11 ወራት በጉዳት ምክንያት
ከውድድር ርቃ የቆየችው የኦሎምፒክ እና
የአለም ዋንጫ አሸናፊዋ አትሌት አልማዝ
ከድሉ በኋላ ሀትሪክ ጋዜጣና ሀትሪክ ድረ-
ገፅን ጨምሮ ለንደን ለተገኙ ከመላው ዓለም
ለተውጣጡ የሚዲያ አካላት የሰጠችው
መግለጫ ከዚህ በታች ያለውን ይመስላል።
ድሉን በተመለከተ ስለተሰማት ስሜት …
“የተለያየ ደስታ ስሜት ተሰምቶኛል፤ ሪዮ
ኦሎምፒክ ላይ ሪከርድ ሰብሬ ያሸነፍኩት ግን
እጅግ በጣም የተደሰትኩት ዛሬ ነው።”
አንድ ዓመት ሙሉ በጉዳት ስለመቆየትዋ
ደስታዬንም ልዩ ያደረገው ይሄ ነው፤
አንድ ዓመት አካባቢ ማለትም ከሪዮ ኦሎምፒክ
በኋላ በጉዳት ምክንያት አንድም ውድድር
አላደረኩም፤ በዚህ ችግር ውስጥ ሆኜ ማሸነፌ
አስደስቶኛል።”
ለኦሎምፒክ ብላ ውድድር ስለመሰረዝዋ
“ለለንደን ዓለም ዋንጫ ልዩ ትኩረት ነው
የሰጠሁት ምክንያቱም አለም ሻምፒዮና ልዩ
ታሪክ ነው። ለአለም ሻምፒዮና ብዬ ሞናኮ እና
ሮም ያሉብኝን ውድድሮች የሰረዝኩትም ለዚህ
ብዬ ነው፤ በውሳኔዬም በጣም ደስተኛ ነኝ።”
የለንደንን የአየር ሁኔታ በተመለከተ
“ወደ ለንደን እንደመጣን የነበረው የአየር
ሁኔታ አገራችን ላይ ስንዘጋጅ ከነበረው ጋር
ተመሳሳይ ነበር፤ ቀዝቃዛ ላይ ሰርተን ቀዝቃዛ
ላይ መሮጥ ከባድ ነበር፤ ዛሬ ግን ቀኑ በጣም
ጥሩ ስለነበር አየሩ አላስቸገረኝም።”
ከኋላ ስለሚከተላት አትሌቶችና ርቀቱን
እንዴት እንደምትከታተለው
“ዕውነት ለመናገር ከኋላዬ እነማን
እንዳሉ በስክሪኑ ጭምር እከታተላለሁ፤
በምን ያህል ርቀት እንዳሉ ነው ማወቅ
ያልቻልኩት እንጂ እከታተላቸው ነበር።
በቀጣይ ስለምታደርገው የ5ሺ ሜ ሩጫን
በተመለከተ … ለውድድሩ ትንሽ ቀን አለው
ከውድድሩ በፊት እንደዚህ አደርጋለሁ ባልልም
ከሌሎች ጋደኞቼ ጋር በመሆን የተሻለ ውጤት
ለማምጣት ጥረት አደርጋለሁ።”
“ውድድሩ ለራሴም ለአገሬም የወርቅ
ሜዳልያ አመጣለሁ ብዩ አስቤ ነበር፤ ነገር ግን
ምኞቴንና ህልሜን እንዳሳካሁ ጉዳት እንቅፋት
ሆኖብኛል፤ የብር ሜዳሊያ አግኝቻለሁ
የመጀመያ ምኞቴና ፍላጎቴ ይህ ባይሆንም
አምላክ ይበቃል ብሎ የሰጠኝን ጉዳት እኔና
አምላኬ ብቻ ስለምናውቀው ነው” ይሄንን ከላይ
የሰፈረውን ቃል የ2017ቱን የለንደን የአለም
አትሌቲክስ ሻምፒዮና የማራቶን ውድድር
በሁለተኛነት ካጠናቀቀ በኋላ 2 ኪ.ሜትር
ርዝመት ባለውና ከ400 በላይ በሚሆን
ሰራተኞች የተገነባው ከ70 ሺህ ቶን በላይ
ሲሚንቶን እንዴት አድርጎ በመላው የለንደኖች
መግለጫና ዋነኛ የቱሪስት መስህብ ከሆኑት
ታላላቅ ድልድዮች አንዱ በሆነው ለንደን ብሪጅ
ታወርስ ላይ ሆኖ በተለይ ለሀትሪክ አስተያየቱን
የሰጠው የብር ሜዳሊያ ለአገራችን ያስገኘው
አትሌት ታምራት ቶላ ነው፡፡ የ2017 የዱባይ
ማራቶን ረቡዕ በመስበር ያሸነፈው የሪዮ
ኦሉምፒክ የነሐስ ሜዳልያ ባለቤት የነበረው
አትሌት ታምራት ቶላ 42 ኪሎ ሜትሩን
በሁለተኛነት ካጠናቀቀ በኋላ ከፍተኛ ድካምና
የጉዳት ስሜት የታየበት ሲሆን ለተወሰኑ
ደቂቃዎችም ራሱን መቆጣጠር አቅቶት
በዊልቸር የህክምና እርዳታ ወደሚያገኝበት
ማዕከል መውሰድንና ህክምና መከታተሉን
ሀትሪክ በቦታው ተገኝታለች፡፡
አትሌት ታምራት ቶላ ሁለተኛውን የብር
ሜዳሊያ ለአገራችን ካስገኘ በኋላ በIAAF እና
በለንደን የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አዘጋጅ
ኮሚቴ ባደረገለት የቀጥታ ግብዣ ለንደን
የሚገኘው የሀትሪክ ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር
ጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ ውድድሩ እንዴት ነበር?
በማለት ከአትሌት ታምራት ቶላ ጋር አጭር
ቆይታ አድርጓል
“ውድድሩ በጣም ጥሩ ነበር፤ ከመነሻው
ለራሴም ለአገሬም ወርቅ አመጣለሁ የሚል
ሃሳቡ ነበረኝ፡፡ መጨረሻ ላይ ግን ጉዳት
ህልሜንና ፍላጎቴን አሰናክሎታል” የሚለው
አትሌት ታምራት ቶላ እስከ “33ኛውና 35ኛው
ደቂቃ ድረስ በጣም በጥሩ ሁኔታ ላይ ነበርኩ
ከ35ኛው ደቂቃ በኋላ ግን የጠነከረ የህመም
ስሜት ተሰማኝ፡፡ በተለይ ወደ መጨረሻ ላይ
በጣም የጉዳት ስሜት ስለተሰማኝ ውድድሩን
የምጨርስ ሁሉ አልመሰለኝም ነበር፤ ያም
ቢሆን ግን ህመሜንና ስቃዬን ችዬ ለአገሬ የብር
ሜዳሊያ አምጥቻለሁ” ያለው አትሌት ታምራት
ቶላ አስተያየቱን ሲቀጥል “ውድድሩን ስጨርስራሱ አላመንኩም፡፡ የነበረብኝን ህመምና ስቃይ
የምናውቀው እኔና ፈጣሪዬ ብቻ ነን” ብሏል፡፡
ህመሙና ጉዳቱ ምን እንደሆነ የተጠየቀው
ታምራት ለጥያቄው ምላሹን ሲሰጥ “እግሬ
ላይ ወይም የአቺላስ ቴንዲንሲ ጉዳት ነበረብኝ፡
፡ ጀርመን ድረስ ሄጄ ታክሜ ነበር፤ ነገር
ግን ሙሉ በሙሉ መፍትሔ አላገኘሁም፡
፡ ለዛሬ ውድድር ከመቅረቤ በፊት ማምሻውን
በበረዶ ስታሽና የህክምና ክትትል ሳደርግ
ነው ያመሸሁት፡፡ የገጠመኝ ጉዳት ህልሜን
አጨናገፈው፤ ፍላጎቴ ይሄ አልነበረም፡፡ ምንም
ማድረግ አልችልም፤ ይሁን የተባለው ይሆናል”
የሚለው የለንደኑ ኦሎምፒክ አትሌቲክስ
ሻምፒዮና የብር ሜዳሊያ ባለቤቱ አስተያየቱን
ሲቀጥል “መጀመሪያ ላይ እንዳያችሁት በጣም
ደህና ነበርኩኝ፤ የጠነከረ የህመም ስሜት
እየተሰማኝ የመጣው ወደ 33ኛው ኪ.ሜትር
አካባቢ ነው፤ እግሬ ላይ ውጋት ነገር ይሰማኝ
ነበር፡፡ ከዚያ በፊት ደህና ነበርኩ፤ ያም ቢሆን
ግን ከህመሜ ጋር እየታገልኩ በሌላ በኩል ለአገሬ ውጤት ለማምጣት ታግያለሁ” የሚለው
አትሌቱ “እኔ እንኳን የብር ሜዳሊያ ላመጣ
ውድድሩንም እጨርሳለሁ ብዬ አላሰብኩም
ነበር፤ ህመሜን ውጬ ስቃዬን ችዬ ነው
ውድድሩን በሁለተኛነት ያጠናቀቅኩት” ብሏል፡፡
“በውድድሩ ሁለተኛ በመውጣት ያገኘሁትን
የብር ሜዳሊያ ልክ ውጤት እንዳጣሁ ያህል
አድርጌ አላስብም፡፡ ከገጠመኝ ጉዳት አንፃር ትልቅ
ውጤት ነው” የሚለው አትሌት ታምራት ቶላ
“እኔ እንደውም ከአራት ወራት በፊት መሮጥ
የፈለግኩት ለንደን ላይ በ10 ሺህ ነበር፤ 10ሺህ
ሜትር ላይ ጥሩ ስለነበርኩኝ ፍላጎቴ 10ሺህ
ነበር፤ ነገር ግን በገጠመኝ ጉዳት ምክንያት
ፊልዴን ቀይሬ ወደ ማራቶን ገብቻለሁ፡፡ ያም
ቢሆን አያስከፋም፤ ለራሴም ለአገሬም ትልቅ
ውጤት ነው ያስመዘገብኩት” በማለት አትሌት
ታምራት አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡
በማራቶን ሁለተኛ መውጣት ያውም በአለም
ሻምፒዮን ትልቅ ውጤት ነው፡፡ ከህመምህ ጋር
እየታገልክና እየተሰቃየህ ካሸነፍክ በኋላ የነበረህ
ስሜት እንዴት ነበር? በሚል ቀረበለት ጥያቄ
አትሌት ታምራት ሲመልስ “እኔ እንኳን መሮጥ
መራመድ እስከማልችል ድረስ ነበር የህመም
ስሜት ይሰማኝ የነበረው” ብሏል፡፡
ታምራት ቶላ 42 ኪሎ ሜትሩን
በሁለተኛነት ካጠናቀቀ በኋላ ከፍተኛ ድካምና
የጉዳት ስሜቱን መቆጣጠር አቅቶት በዊልቸር
የህክምና እርዳታ ወደሚያገኝበት ማዕከል
መውሰዱን አስመልክቶ ሲናገርም “ከአቅሜ
በላይ እስኪሆን ድረስ ነው የሮጥኩት፡፡ የሆነ
ሰአት ላይ በጣም ስለታመምኩ ከኋላዬ ማነው
መጥቶ የሚቀድመኝ የሚል ስጋት ውስጥም
ሆኜ ነው ውድድሬን የጨረስኩት፡፡ እግሬን ሁሉ
መዘርጋት ሁሉ አቅቶኝ ነበር፡፡ ወደ ውድድር
የገባሁት አሸንፋለሁ ብዬ የነበረ ቢሆንም
በጉዳት ምክንያት አልተሳካልኝም፤ ያም ቢሆን
በኦሎምፒክና በአለም ሻምፒዮና ለአገሬ አቅሜ
የሚችለውን ለማድረግ ሞክሬያለሁ፤ ጉዳት
ባይገጥመኝ ከዚህም በላይ ወርቅ ማምጣት
እችል ነበር፤ እንደዛም ቢሆን ይህንን ሜዳሊያ
በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ፤ ውጤት ያጣሁ ያህልም
አይሰማኝም፤ በቀጣይ ጠንክረን ሰርተን ደግሞ
የተሻለ ነገር እናመጣለን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ”
ሲል በለንደን ከሚገኘው የሀትሪክ ጋዜጣ
ማኔጂንግ ኤዲተር ጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ ጋር
የነበረውን ቆይታ አጠናቅቋል፡፡