የመቐለ 70 እንደርታው አጥቂ አማኑኤል ገብረሚካኤል ከውጭ ሃገር ክለቦች በተለይ ደግሞ ከግብጹ ክለብ ኢኤንፒፒአይ አማላይ ጥሪ ቢቀርብለትም ተጫዋቹ ግን ሳይቀበለው ቀርቷል።
ለብሔራዊ ግዴታ ሌሴቶ የነበረው አጥቂው ከሌሴቶ ከተመለሰ በኋላ ዝውውሩን ያደርጋል ተብሎ ቢጠበቅም ዝውውሩን በግል ጉዳይ ሳይቀበለው መቅረቱን እና ድርድሩ መቋረጡን የተጫዋች ወኪል ተሾመ ፋንታሁን አስታውቋል።
የግብጽ ሊግ የተጫዋቾች ዝውውር ሰኞ ጠዋት የሚጠናቀቅ ሲሆን ለዝውውሩ የሚረዱ የወረቀት ሥራዎች ከሰኞ በፊት መጠናቀቅ ነበረባችው፤ ይህም ሳይሆን በመቅረቱ አማኑኤል በዚህ የዝውውር ወቅት ወደ ኤንፒፒአይ አይሄድም ሲል ጉዳዩን የያዘው የተጫዋች ወኪል ገልጿል።