ከጥቂት ሰአታት በፊት ሶስት ተጨዋቾችን ያስፈረሙት መቐለ 70 እንደርታዎች የግራ መስመር ተመላላሹን አስናቀ ሞገስን ማስፈረማቸው በይፋዊ ገፃቸው አስታውቀዋል ።በያዝነው የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት
መከላከያን ለመቀላቀል ከስምምነት ደርሶ የነበረው አስናቀ ሞገስ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያደረገውን የፎርማት ለውጥ በመንግስት ውድቅ መደርጉን ተከትሎ መከላከያ በፕሪምየር ሊጉ እንደማይሳተፍ ስለተረጋገጠ ከጦሩ ጋር ሊለያይ ችሏል።
የመቐለ 70 አንደርታ የክረምቱ 9ኛ ፈራሚ የሆነው አስናቀ ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ከባህርዳር ከተማ ጋር ያሳለፈ ሲሆን፣ከዚህ ቀደምም ለኢትዮጵያ ቡና መጫወቱ ሚታወስ ነው።