አጥቂው አቡበከር ናስር ኢትዮጵያ ቡና ከአዳማ ከተማ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ ከጉዳቱ አለማገገሙ ተከትሎ በጨዋታው የማይሰለፍ ተጫዋች ሆኗል።
ከፋሲል ከተማ ጋር በነበረው ጨዋታ ከግብ ጠባቂው ሚካኤል ሳማኪ ጋር ተጋጭቶ ጉዳት ያስተናገደው ተጫዋቹ ለነገው ጨዋታ እንደማይደርስ እርግጥ ሆኗል። የሸገር ደርቢን ጨምሮ ሳይሰለፍ የቀረው አቡበከር ናስር ቀለል ያለ ልምምድ እየሰራ እንደሆነ እና የነገውን ጨዋታ ለመመልከት ወደ አዳማ እንደሚያመራ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።