በዘንድሮው የውድድር ዓመት ስማቸው በስፋት ከተጫዋች ደሞዝ ጋር ሲነሳ የቆዩት አዳማ ከተማዎች ከተጫዋቾቻቸው ጋር መለያየታቸውን ቀጥለዋል ።
የአዳማ ከተማ ተጫዋቾች ማረፊያቸው በቀድሞው አሰልጣኛቸው አሸናፊ በቀለ ወደ ሚመራው ሀድያ ሆሳዕና ነብሮቹን በማድረግ ላይ ይገኛሉ ።
ከደቂቃዎች በፊት በአዳማ ከተማ የኋላ ክፍል ላይ ጥሩ ብቃቱን ሲያሳይ የቆየው ሱሌይማን ሀሚድ ነብሮቹን የተቀላቀለ ተጫዋች ሆኗል ።
- ማሰታውቂያ -
በሌላ በኩል በወላይታ ድቻ እና አዳማ ከተማ ያለፉትን ዓመታት ያሳለፈው ሀይሌ እሸቱ ማረፊያውን ሀድያ ሆሳዕና አድርጓል ።
ሀድያ ሆሳዕና ወደ ዝውውሩ ዘግየት ብለው ቢገቡም በዛሬው ዕለት አምስት ተጫዋቾችን ማስፈረም ችለዋል ።