በአሰልጣኝ ዲዲዬ ጎሜዝ እየተመሩ ቡድናቸውን በማጠናከር የተጠመዱት ቡናዎች ኡጋንዳዊውን ግብ ጠባቂ ኢስማኤል ዋቴንጋን ማስፈረማቸውን ይፋ ኣድርገዋል።ከቫይፐርስ ጋር የኡጋንዳ ፕሪሜየርሊግ ዋንጫን ማንሳት የቻለው ዋቴንጋ ዲዲዬ ጎሜዝ የ2011 ኢትዮጵያ ፕሪሜየርሊግ ዋንጫን ለማንሳት በሚያደርጉት ግስጋሴ ኣጋዥ እንደሚሆናቸው ይገመታል።
ተመስገን ካስትሮ፣ተካልኝ ደጀኔ እና ኣልሃሰን ካሉሻን ማስፈረም የቻሉት ጎሜዝ አምና ቡድኑ ላይ ከታዩት ወጣት ተጨዋቾች ጋር በማጣመር ለዋንጫ ተፎካካሪ ቡድን ሊሰሩ እንደሚችሉ ይገመታል።የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ባህርዳር ላይ እያካሄዱ ሚገኙት ኢትዮጵያ ቡና በከተማው ይዘጋጃል ተብሎ በሚጠበቀው አማራ ሲቲ ካፕ ሊሳተፋ ይችላሉ።