ኢንተርናሽናል አልቢተር ባምላክ ተሰማ ከሁለት ዓመት በኋላ በኳታር አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የ 2022 የዓለም ዋንጫ ከታጩት ስድስት አፍሪካውያን ዳኞች ውስጥ ቀዳሚው መሆን ችሏል ።
ኢንተርናሽናል አልቢተር ባምላክ ተሰማ ከአልጄርያው ሙስተጠፋ ጎርባል ፣ ከሞሮኮው ሬድዋን ጄይድ ፣ ከግብፁ ኦማር ሞሐመድ ፣ ከሴኔጋሉ ማጉቴ ንዳዬ እንዲሁም ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎው ንጋምቦ ንዳላ የታጩት ስድስት ዳኞች መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል ።
ኢንተርናሽናል አልቢተር ባምላክ ተሰማ ማጉቴ ንዳዬ እንዲሁም ንጋምቦ ንዳላ በኳታሩ የዓለም ዋንጫ እንሚሳተፉ ትልቁን ግምት አግኝተዋል ።