በዘንድሮ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት መከፈቱን ተከትሎ በርካት ተጫዋቾችን ያስፈረመው ወልዲያ እግር ኳስ ክለብ ካስፈረማቸው የቡድኑ ተጨዋቾች ጋር አሁንም ከስምምነት ላይ መድረስ አለመቻሉን ሀትሪክ ስፖርት ድህረ ገፅ ከውስጥ ምንጮችዋ ማረጋገጥ የቻለቸው፡፡ ከክለቡ ጋር ከዚህ በፊት ልምዳቸውን አቋርጠው የ1ዓመት ከ 5ወር ደሞዛቸው እንዲከፈላቸው ከጠየቁት ተጫዋቾች መካከል ፍፁም ገብረማርያም ፣ብሩክ ቃልቦሬ ቢያድግኝ ኤሊያስ ፣ ምንያህል ተሾመ ሲሆኑ ከትናንትና በስቲያ ሌላው ከቅዱስ ጊዮርጊስ ያስፈረሙት ተስፋዬ አለባቸው (ቆቦ) ተቃዋሞውን መቀላቀሉ እረግጥ ሆኗል፡፡
ከክለቡ አካባቢ አየተሰማ እሚገኘው ክለቡ ተጫዋቾቹ የጠየቁት ገንዘብ ከ10 ሚሊየን ብር በላይ በመሆኑ የክለቡን የፋይናንስ አቅም እንደሚያዳክም እና የጠየቁት ገንዘብ እንደማይከፍላቸው እና ተጨዋቾቹ ያነሱትን ተቃውሞ በመተው ወደ ልምምዳቸው እንዲመለሱ ይህን እማያደርጉ ከሆነ ክለቡ በተጫዋቾቹ ላይ ቅጣት እንደሚያስተላለፍ ሀትሪክ ድህረ ገፅ ከክለቡ አካባቢ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማሉ፡፡
በተጨዋቾች ውዝግብ ውስጥ የሚገኘው ወልድያ ስፖርት ክለብ የአንድ ተጨዋችን ውል ሲያድስ ሌላ አንድ ተጨዋችን አስፈርሟል
ለበርካታ አመታት በወልድያ ስፖርት ክለብ በተጨዋችነት ያገለገለውን የኤፍሬም ጌታሁን (አብይ) ውል ሲያድስ የቀድሞውን የሀረር ሲቲ ፣የኢትዮ-ኤሌክትሪክእና የአዲስ አበባ ከተማ ተጨዋች የነበረውን አማረ በቀለን ዛሬ ከሰዓት በኃላ በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን በመገኘት ማስፈረም ችሏል፡፡