በዚህ አመት ወላይታ ድቻ አሰልጣኙን በውጤት ማጣት ካሰናበቱ ክለቦች ቀዳሚው ሆኗል።
በዘንድሮው አመት ከአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ጋር በመለያየት የቀድሞው ዲላ እና ደቡብ ፖሊስ አሰልጣኝ የነበሩት አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራን የቀጠሩት ወላይታ ድቻ ክለባቸው በተጠበቀው መልኩ እየሄደ አለመሆኑን ተከትሎ ከብዙ ውዝግቦች በኋላ ከአሰልጣኛቸው ጋር ዛሬ በመወያየት በስምምነት መለያያታቸው ሀትሪክ ስፖርት ከስፍራው ያገኘችው መረጃ ጠቁሟል። ወላይታ ድቻ በዚህ አመት ከስምንት ጨዋታ ስድስት ነጥብ አግንቶ በሶስት የግብ እዳ በሊጉ ግርጌ ላይ ተቀምጧል።