በኢትዮጵያ እግር ኳስ ስማቸውን በወርቅ ብዕር ካፃፋ ተጨዋቾች ዝርዝር ውስጥ ሚጠቀሰው አዳነ ግርማ ወልቂጤ ከተማን ተቀላቅሏል።
ባሳለፍነው ዓመት ከሃዋሳ ከተማ ጋር ያሳለፈው አዳነ ግርማ የወልቂጤ ከተማ የክረምቱ 16ተኛ ፈራሚያቸው መሆን ችሏል።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በ2013 የአፍሪካ ዋንጫ ከ31 ዓመታት በኃላ ተሳትፎ ሲያደርግ ውድድሩ ላይ ብቸኛዋን ከ31 ዓመታት በኃላ የተገኘች ግብ ያስቆጠረው አዳነ ግርማ በጊዮርጊስ እና በሃዋሳ ቤት ያካበተውን ልምድ አዲስ አዳጊውን ወልቂጤ ከተማን ሊያግዘው አንደሚችል ይገመታል።