በ20ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ትግራይ ስታድየም ላይ ወልዋሎ ና መከላከያን ያገናኘው ጨዋታ በባለ ሜዳዎቹ ወልዋሎዎች እሸናፊነት ተጠናቋል።ወልዋሎዎች ባሳለፍነው ሳምንት ደቡብ ፖሊስን ካሸነፈው ቡድን እብዱራህማን ፋሴይኒን በእንየው ካሳሁን፣ብርሃኑ እሻሞን በኤፍሬም ሃይለማርያም፣ኤፎቤ ችዞባን በራችሞንድ ኦዶንግ በአጠቃላይ ሶስት ቅያሬዎችን ሲያደርጉ፤የስዩም ከበደው መከላከያ በበኩሉ በደደቢት ከተሸነፈው በድን በተመሳሳይ ሶስት ቅያሬዎችን ማለትም አቤል ማሞን በይድነቃቸው ኪዳኔ፣አበበ ጥለሁን በአዲሱ ተስፋዬ እንዲሁም ሳሙኤል ታዬን በተመስገን ገብረኪዳን ቀይረው ወደ ሜዳ ገብተዋል ።
የመከላከያ የኳስ ቁጥጥር ብልጫ እና የወልዋሎ የግብ ሙከራ የበላይነት በታየበት የመጀመርያው አጋማሽ ጥሩ ፋክክር ታይቶበታል።ቀጥተኛ የማጥቃት መንገድ በመያዝ በአጭር ቅብብል ወደ መስመር በሚወጡ ኳሶች እድሎችን መፍጠር የቻሉት ወልዋሎዎች ጨዋታው በተጀመረ በአንደኛው ደቂቃ በሪችሞንድ ኦዶንግ የጨዋታው የመጀመርያ ሙከራን ማድረግ ችሏል።ከመስመር በሚነሱ ኳሶች የቀጠሉት ወልዋሎ ከመሃል ሜዳ በጥሩ ቅብብል ወደ ቀኝ መስመር የተላከውን ኳስ እንየው ካሳሁን ኣሻምቶት ኤፍሬም እሻሞ ወደ ጎል ቢመታውም ይድነቃቸው ኪዳኔ ግብ ከመሆን እድኖታል።የግብ እድሎችን መፍጠራቸውን የቀጠሉት ቢጫ ለባሾቹ በ19ኛው ደቂቃ አማኑኤል ጎበና በረዥሙ የላከው የተመጠነ ኳስ ሪችሞንድ ኦዶንግ አግኝቶ በጥሩ እጨራረስ ወልዋሎን ቀዳሚ ማድረግ ችሏል።በተደጋጋሚ ከሚጠቀሙበት 4-4-2 ወደ 4-2-3-1 ቀይረው ወደ ሜዳ የገቡት መከላከያዎች ኳስን ከተጋጣሚያቸው በተሻለ መልኩ ቢያንሸራሽሩም የጠራ የግብ እድል መፍጠር እልቻሉም።በመጀመርያው አጋማሽ በበሃይሉ ግርማ ና በቴዎድሮስ ታፈሰ ኣማካኝነት ከርቀት ሙከራዎችን ቢያደርጉም አብዱላዚዝ ኬይታን ሚፈትኑ እልነበሩም።ወልዋሎዎችም መሪነታቸውን ለማስፋት ሙከራዎችን እድርገዋል በተለይም እንየው ካሳሁን ከሪችሞንድ ኦዶንግ አንድ ሁለት ተቀባብለው እንየው በፍጹም ቅጣት ሳጥን በቀኝ በኩል ያገኘውን ኳስ ቢመታውም የግቡን የጎን መረብ ታኮ፣ ወደ ውጭ ወጥቷል።
በሁለቱም ቡድን በኩል ጥሩ ጨዋታ ባልታየበት ሁለተኛው አጋማሽ ወልዋሎዎች ውጤቱን ለማስጠበቅ መከላከያ አቻ የምታደርጋቸውን ግብ ለማግኘት ጥረት ሲያደርጉ ታይቷል።አሰለጣኝ ስዩም ከበደ ቴዎድሮስ ታፈሰን በፍፁም ገብረማርያም በመተካት ሁለት አጥቂዎችን ፊት በማስቀመጥ ከቆሙ ኳሶችና በረጃጅም ኳሶች እድሎችን ለመፍጠር ቢሞክሩም አቻ እምታደርጋቸውን ግብ ሳያገኙ ቀርተዋል።አብዛኛው የሁለተኛው እጋማሽ ክፍል በመከላከል ያሳለፋት ወልዋሎዎች አልፎ አልፎ በአማኑኤል ጎበና እንዲሁም በኤፍሬም እሻሞ አማካኝነት ሙከራዎችን አድርገዋል።
- ማሰታውቂያ -
ውጤቱን ተከትሎ ወልዋሎ አዲግራት ዮንቨርሲቲ ደረጃውን ከ 8ኛ ደረጃውን ወደ 5ኛ ከፍ ሲያደርግ መከላከያ ወደ ወራጅ ቀጠናው ሚያደርገውን ጉዞ እስቀጥሏል።