ዛሬ ቀጥሎ በዋለው ቱር ሩዋንዳ ኢትዮጵያዊው በረከት ደሳለኝ ተከታዩን ሙጊሻ ሞይዝ በኣንድ ሰከንድ በመቅደም የመጀመርያ ኢትዮጵያዊ ቱር ሩዋንዳ ያሸነፈ መሆን ችሏል።
108 ኪሎ ሜትር በሸፈነው የዛሬው ውድድር ከበረኸት ውጪ ውድድሩ ላይ የተሳተፋት ተመስገን ወዲ ብሩ 6፣ዘርኣይ ወልደኣረጋይ 12፣ሙሉ ሃይለሚካኣል 19 ወጥተዋል።በቡድን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ሲመራ የዳገት ኮከቡ ሌላኛው ኢትዮጽያዊ ሙሉ ሃይለሚካኤል ዛሬ በተካሄደው ውድድርም የዳገት ማልያውን ኣስጠብቆ መውጣት ችሏል።