በካፍ ኮንፌደሬሽን ካፕ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ተሳታፊ የሚሆኑት ኢትዮጵያን የወከሉት ወላይታ ድቻ እና ቅ/ጊዮርጊስ ተጋጣሚዎቻቸው ታወቁ። በዚህም መሰረት ወላይታ ድቻ ከታንዛኒያው ያንግ አፍሪካ ጋር የተደለደለ ሲሆን ቅ/ጊዮርጊስ በአንፃሩ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎውን ካራ ብራዛቪልን የሚገጥም ይሆናል።
ወላይታ ድቻ ለዚህ ውድድር የበቃው በአንደኛው ዙር የግብፁን ሀያል ክለብ ዛማሌክን በደርሶ መልስ ውጤት በማሸነፍ ሲሆን ቅ/ጊዮርጊስ በበኩሉ በሻምፒዮንስ ሊጉ በዩጋንዳው ኬሲሲኤ በድምር ውጤት 1-0 ተሸንፎ በመውደቁ ወደ ምድብ ድልድሉ መግባት ሳይችል ቀርቶ ለዚህ ውድድር ደርሷል።
ወላይታ ድቻ የመጀመሪያውን ጨዋታ ወደ ታንዛኒያ ተጉዞ ከመጋቢት 28-30 (እ.ኤ.አ ሚያዝያ 6-8) ባሉት ቀናት የሚያከናውን ሲሆን የመልሱ ጨዋታ ደግሞ ከ10 ቀናት በኋላ ከሚያዚያ9-10 ( እ.ኤ.አ ሚያዝያ 17-18) ሀዋሳ ላይ የሚደረግ ይሆናል። ቅ/ጊዮርጊስ ደግሞ የመጀመሪያ ጨዋታውን አ/አ ላይ በተመሳሳይ ቀን የሚያደርግ ሲሆን የመልሱን ጨዋታ ወደ ኮንጎ አምርቶ የሚያከናውን ይሆናል።
ሁለቱም ቡድኖች ጨዋታዎቻቸውን የሚያሸንፉ እና የሚያልፉ ከሆነ 16 ቡድኖች ወደሚሳተፉበት የምድብ ድልድል መቀላቀል ይችላሉ። የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ሙሉ ጨዋታዎች ዝርዝር ከዚህ የሚከተለው ነው።