በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድንቅ ብቃቱን በማሳየት በስፖርት አፍቃሪው ዘንድ እውቅናን ያተረፈው በረከት አዲሱ ከአንድ ዓመት ክለብ አልባ ቆይታ በኃላ በአዲሱ የአርባምንጭ ከተማ አሰልጣኝ እዮብ ማለ ወደ ጥሪ ቀርቦለት ለ1 ዓመታት መፈረሙ ታውቋል።
ተጫዋቹ ከሲዳማ ቡና ጋር በ2009 በአንዳንድ ችግሮች ባለመስማማት የተለያየው በረከት አዲሱ ለአንድ አመታት ክለብ አልባ ሆኖ መቆየቱ እሚታወስ ነው።
በረከተ አዲሱ ከዚህ ቀደም ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ለቅዱስ ጊዮርጊስ ፣አዳማ ከተማ፣ለሲዳማ ቡና መጫወቱ እሚታወስ ነው