በኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ 21ኛ ሳምንት ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ሀዋሳ ተጉዞ ሀይቆቹን ሀዋሳ ከተማን ዛሬ 9ሰዓት ለመግጠም ሰዓታት በቀሩበት ሰዓት ጨዋታው በፀጥታ ስጋት ምክንያት የክልሉ ፖሊስ ሀላፊነት እንደማይወስዱ በመግለፃቸው ጨዋታው እንደማይደረግ ታውቋል።
ትናንት በተመሳሳይ ሰዓት ሊደረግ ታስቦ የነበረው የደቡብ ፖሊስ እና ወላይታ ድቻ ጨዋታ ከጨዋታው መጀመር በፊት በደጋፊዎቻቸው እረብሻ ጨዋታው ሲሰረዝ ወላይታ ድቻ ለፌዴሬሽኑ ባስገባው ጨዋታው ወደ ገለልተኛ ሜዳ ይቀየርልን የሚል ደብዳቤ ተከትሎ ጨዋታው ወደ ሌላ ግዜ ተላልፏል።