በ4ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ ወደ ድሬዳዋ ያቀናው መሪው ደደቢት አንድ ነጥብ ይዞ መመለስ ችሏል፡፡
ድሬዳዋ 28’c በሆነ ሞቃታማ የአየር ሁኔታ በነበረው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ አዲስ በተሰራው የካታንጋ ቦታ በርካታ ተመልካቾች ተገኝተው ተከታተለውታል፡፡
- ማሰታውቂያ -
ልክ 10፡04 ሲል የጀመረው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ የመጀመሪያው አጋማሽ ከመሀል ክፍል ኳስን ከማንሸራሸር ያለዘለለ ከአንድ በላይ የጎል ሙከራ ያልታየበት ነበር፡፡
28’ደቂቃ ላይ የደደቢቱ የመሀል ተከላካይ ብርሀኑ ቦጋለ በጉዳት በሰለሞን ሀብቴ ለመቀየር ተገዷል፡፡ የመጀመሪያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ 4ደቂቃ በተጨመረበት ሰዓት ላይ ሱራፌል ዳንኤል16:50 ውስጥ የሰራው ስህተት ተጠቅሞ አቤል ያለው ለማግባት ያደረገውን ጥረት የድሬደዋ ግብ ጠባቂ ሳምሶን አሰፋ ሊከሽፍ ችሏል፡፡
በሁለተኛው አጋማሽ እንደ መጀመሪያው የጨዋታ ክፍለ ግዜ እንብዛም የጎላ ሙከራ ያለተደረገበትና ጥንቃቄ የበዛበት ጨዋታ ነበር፡፡
74 ኛው ደቂቃ ላይ አሰልጣኝ ዘላለም ሸፈራዉ በሜዳው እንደ መጫወቱ 3ነጥብ ለማግኘት የተከላካይ ቁጥሩን በመቀነስ ዘነበ ከበደን በ2009 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ኮከብ ግብ አግቢ የነበረውን ዘካሪያስ ፍቅሬን ቀይሮ፡ቢያስገባም የደደቢትን የተከላካይ ክፍልን ሰብሮ ለመግባት አልቻሉም፡፡ ጨዋታውም 0-0 በሆነ ውጤት ሊጠናቀቅ ችሏል፡፡
የደረጃ ሰንጠረዥ