የመቐለ 70 እንደርታ ከእዲስ ፈራሚ ካሉሻ እልሃሰን ለህክምና ወደ ጋና ይሄዳል
በያዝነው የክረምት ተጨዋቾች ዝውውር ሻምፒዮኖቹን የተቀላቀለው ካሉሻ ኣልሃሰን ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት ወደ ጋና ሊያቀና ነው።ላለፋት ቀናት የሻምፒዮኖችን ስብስብ በመቀላቀል ልምምዱን ሲያደርግ የቆየው ካሉሻ ጉልበቱ ላይ ባጋጠመው ጉዳት ከባድ መሆኑ ተከትሎ ወደ ሃገሩ ጋና ለህክምና ሚሄድ ይሆናል።
ከእዳዲስ ፈራሚዎቹ ፅዮን መርእድና እለልኝ እዘነ ጋር የተለያዩት መቐለ 70 እንደርታ እሁንም በተመሳሳይ ከጋናዊው ካሉሻ ጋር ሚኖራቸው ቆይታ እጠራጣሪ ሆኗል።