ዛሬ በተካሄደ የሰበታ ከተማ ና ወላይታ ድቻ ጨዋታ ጅማሮውን ያደረገው የ6ተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ነገ ስድስት ጨዋታዎችን ያስተናግዳል።በፕሪምየር ሊጉ ዓብይ ኮሚቴ ትእዛዝ መሰረት እድሳቱን አጠናቆ ለውድድር ዝግጁ በሆነው ወልቂጤ ስታድየም ሚካሄደው የወልቂጤ ከተማ ና ስሁል ሽረ ጨዋታ በዚህ መልኩ ዳስሰን አቅርበንላችኃል።
ወልቂጤ ከተማ ከ ስሁል ሽረ
የጨዋታ ቀን: ቅዳሜ ታህሳስ 25/2012
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር:
ቦታ: ወልቂጤ ስታድየም
በ5ኛው ሳምንት ወልቂጤዎች ወላይታ ድቻን ሲያሸንፋ ስሁል ሽረዎች በበኩላቸው በመጨረሻ ደቂቃ በተቆጠረባቸው ግብ ከአዳማ ከተማ ጋር እኩል ተለያተው ለነገው ጨዋታ ይቀርባሉ።በመሃላቸው የ3 ነጥብ ልዩነት ይዘው ሚገናኙት ሁለቱ ቡድኖች በነገው ጨዋታ በርካታ ተጨዋቾቻቸውን በጉዳት እና በግል ምክንያት ሚያጡ ይሆናል።ወልቂጤዎች አሳሪ ኣልማህዲ፣ቶማስ ምህረቱ፣አዳነ ግርማን ሲያጡ ስሁል ሽረዎች በበኩላቸው ሙሉኣለም ረጋሳ፣ወንድወሰን ኣሸናፊ እና ሃይለኣብ ሃይለስላሰን ማይጠቀሙ ይሆናል።
መስመር ላይ ትኩረት አድርገው ሚጫወቱት ወልቂጤዎች ከጫላ ተሺታ፣ሄኖክ አወቀ በሚነሱ እና ጃኮ አራፋትን ትኩረት ያደረጉ ኳሶችን በመጠቀም እድሎችን ለመፍጠር ሊጫወቱ እንደሚችሉ ይገመታል።ስሁል ሽረዎች በበኩላቸው ከሜዳቸው ውጪ ሲጫወቱ ሚከተሉትን ወደ ኃላ አፈግፍጎ በመልሶ ማጥቃት እድሎችን የመፍጠር የጨዋታ ስልት ይተገብራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
- ማሰታውቂያ -
በወልቂጤዌች በኩል ባለፈው ጨዋታ ግብ ያስቆጠረው ጫላ ተሺታ እና ጃኮ ኣራፋት በስሁል ሽረዎች የክለቡ ኮከብ ግብ አስቆጣሪ ዲድየር ሌብሪ እና ከቅጣት የተመለሰው ተከላካዩ ዮናስ ግርማይ ከሁለቱም ቡድኖች በኩል በነገው ጨዋታ ልዩነት ሊፈጥሩ እንደሚችሉ ይገመታል።