ድሬድዋ ከተማ የአማካይ ተከላካይ የሆነውን አስጨናቂ ሉቃስ በአንድ አመት ኮንትራት ማስፈረም ችሏል። የሐዋሳ ከነማ ኮንትራቱን ዘንድሮ የጨረሰው አስጨናቂ ከዚህ በፊት ለደቡብ ፖሊስ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ተጫውቶ ማሳለፉ ይታወሳል ።
ድሬዳዋ ከተማ በመፈረሜ ደስ ብሎኛል ያለው አስጨናቂ ” የፍቅር ከተማ ከሆነች ድሬ ጋር ጥሩ ነገር ለመስራት ነው አላማዬ” ብሏል ። በሚቀጥለው አመት ጥሩ የፕሪሚየር ሊግ ተፎካካሪ ለመሆን ያለመው ድሬድዋ ከተማ በሚቀጥሉት ጊዜያትም አዳዲስ ተጫዋቾችን ያስፈርማል ተብሎ ይጠበቃል ።
ድሬድዋ ከተማ የዘንድሮው የውድድር ዓመት በኮሮና ቫይረስ እስከ ተቋረጠበት ድረስ ሊጉን በአስራ ሰባት ጨዋታዎች ሀያ አንድ ነጥቦችን ሰብሰቦ ከወራጅ ቀጠናው በሁለት ነጥቦች ብቻ ርቀው ተቀምጠው ነበር ።