አሰልጣኝ ውበቱ አባተ – ሰበታ ከተማ
• ስለ ጨዋታው
የቡድኑ ፍላጎት የሚያሟላ ነገር ይዘን ለምቅረብ እየሞከርን ነው :: ከማሸነፋቸን በላይ ለማሸነፍ የሄድንበት መንገድ ጥሩ ነው ብዬ ነው የማስበው እንደ አጠቃላይ ግን ቡድኔ መሻሻል አለው ለእኔ መልካም ጨዋታ ነበር ::
- ማሰታውቂያ -
• በሁለተኛው አጋማሽ ላይ መከላከል ላያ አተኩራችሃል ለምንድነው ?
አሁንም በምንፈልገው አጨዋወት ውስጥ መዋዥቅ አያለሁ በተለይም ከእረፍት በሃላ በነበረው እንቅስቃሴ ከሃላ መስርትን ከመውጣት ይልቅ ተደጋጋሚ ኳሶች ወደ ፊት ይለቀቁ ነበር ያም ይመስለኛል ::
ከሌሎች ጨዋታዎች የተሻለ ነገር ነው የነበረው በሂደት የሚስተካከሉ ነገሮች ይኖራሉ ::
አሰልጣኝ ገ/ክርስቶስ ቢራራ – ወላይታ ዲቻ
• ስለ ጨዋታው
ጨዋታው ሁለት ገፅታ ነበረው ከእረፍት በፊት ተጫዋቾቼ ይበልጥ ወደ ሃላ አፈግፍገው ነበር :: ከእረፍት በሃላ ግን ያንን አርመን የተሻለ ቡድን ይዘን ለመቅረብ ችለናል ::
ነገር ግን ከእረፍት በፊት ይህንን አጨዋወት ይዘን ብንገባ ኖሮ የተሻለ ነገር ይመዘገብ ነበር :: ያ ነገር ከመፈጠሩ በፊት አንድ ግብ ተቆጥሮብን ጨዋታው በዛው ሊጠናቀቅ ችሏል ::
ከእረፍት በፊት ሁለት የመስመር አማካዮቼ ከሃላ የሚነሱ ወደ ፊት መምጣት አለመቻላቸው ጥሩ እንዳንሆን አድርጎናል ::
• ሽንፈቱ የመጣው በእናንተ ድክመት ነው ወይስ በተጋጣሚ ጥንካሬ ?
እኔ ጥንካሬም ነው ድክመትም ነው አልለውም ምክንያቱም ፍፁም ቅጣት ምት ተሰጠ የተገኘውን አጋጣሚ መጠቀም ስለቻሉ ብቻ ነው ሊያሸንፉን የቻሉት ::