አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው – ጅማ አባጅፋር
ስለጨዋታው
ከሊጉ መሪ ቡድን ጋር ነው የተጫወትነው የኛ ተጫዋቾች ወጣቶች ናቸው ሮጠው ያልጠገቡ ልጆች ነው የሉኝ በሁለቱም በኩል ዕልህ አስጨራሽ እና አጓጊ ጨዋታ የታየበት ነበር። ጥሩ የኳስ ፈሰት ነበር ጨዋታው። ልጆቼ ምን ያህል ተስፋ ሰጪ እንደሆኑም የታየበት ጨዋታ ነበር። መጨረሻ ደቂቃ ላይ እነሱ አጥቅተው ነበር እኛ ደግሞ ውጤቱን ለማስጠበቅ ሰንል ተከላክለን ነበር ተሳክቶልኛል
ሁለትኛ አጋማሽ ላይ የቡድኑ መዳከም
- ማሰታውቂያ -
መዳከም ሳይሆን መጀመሪያ አግብትን እንወጣና ይቺን ወጤት ለማስጠበቅ ካለብን የደረጃ አንፃርም ልጆቼም በጣም ልምድ ስለሌላቸው ነው እኔ ዘንድሮ በነዚህ ልጆች አዲስ ነገር አሳያለሁ።
ሰለ ደጋፊዎች
እኔ ሁልጊዜ ሰለዚህ ደጋፊ የሚገልፀው ቃላት የለኝም ድንቅ የሆኑ ደጋፊዎች ነው ያሉን የሚችሉትን ሁሉ ለዚህ ቡድን የሰጣሉ ። ማለት የምፈልገው ነገር አሁንም ደጋፋቹ አየለየን ለማለት እወዳለው።
የመቐለ 70 እንደርታው አሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ አስተያየት ሳይሰጡ ሜዳውን ጥለው ወጥተዋል።