14ኛው አዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ አራት የከተማዋ ክለቦችና አራት ተጋባዥ ክለቦችን በማሳተፍ ለተከታታይ ሥስት ሳምንታት ይካሄዳል።የአምናው የውድድሩ አሸናፊ ኢትዮጵያ ቡና፣ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና መከላከያ ከተማዋ ክለቦች ባህርዳር ከተማ፣ወልዋሎ፣ሰበታ ከተማ ና ወልቂጤ ከተማ በተገባዥነት ውድድሩ ላይ ሚሳተፋ ክለቦች ናቸው።
የአዲስ አበባ ክለቦችን የፋይናንስ አቅም ለማጠናከርና ወደ ውድድር ከመግባታቸው በፊት አቋማቸው አንዲፈትሹ ለማድረግ በከተማዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት ሚካሄደው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ጥቅምት 22 በአዲስ አበባ ስታድየም ሚጀምር ይሆናል።
የውድድሩ እጣ ማውጣት ሥነ ስርአት ሀሙስ ጥቅምት 13 ከረፋዱ 3:30 በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ይካሄዳል።