አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው መመረጣቸውን ተከትሎ ከ 1ወር ከ9 ቀን በሀኃላ ነገ መጋቢት 19/2009 ዓ.ም ከቀኑ በ10፡00 ሰዓት ጀምሮ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና በኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ዋና አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ መካከል ይፋዊ የፊርማ ሥነ-ስርዓት በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል ይካሄዳል፡፡ የሥራ ውሉን አስመልክቶም ከጋዜጠኞች ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡