የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ 30 ኛ ሳምንት ሰኔ 17 2009 ዓ/ም ከተደረጉ ጨዋታዎች መካከል በሀዋሳ ከተማ እና ኢትዮ ኤሌትሪክ በተደረገው ጨዋታ የውጤት ማስለወጥ ሙከራ ተደርጓል ሲል የጅማ አባቡና እግር ኳስ ቡድን ባስገባው የክስ አቤቱታ ፌዴሬሽኑ ነገ በ10 ሰዓት በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ውሳኔውን በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ ለስፖርት መገናኛ ብዙሐን በላከው ኢሜል መልዕክት አስታውቋል ፡፡
ፈዴሬሽኑ ለመገናኛ ብዙሐን የላከው መልእክት
ለሁሉም የስፖርት መገናኛ ብዙሃን
በ2009 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ዙር እግር ኳስ ውድድር በሀዋሳ ከነማ እና በኢትዮ ኤሌትሪክ መካከል ከተካሔደው ጨዋታ ጋር በተያያዘ ውጤት ለማስለወጥ የተደረገ ሙከራ “አለ” መባሉን ተከትሎ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጉዳዩን ተከታትሎና አጣርቶ ለሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እንዲያቀርብ አንድ አጣሪ ቡድን አቋቁሞአል፣ በመሆኑም ቡድኑ አጣርቶ ያቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በተመለከተ ሀሙስ ነሐሴ 04/2009 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት በኢንተርኮንትኔንተል ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል፡፡
- ማሰታውቂያ -
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን